+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لاَ عَدْوَى وَلاَ طِيَرَةَ، وَلاَ هَامَةَ وَلاَ صَفَرَ، وَفِرَّ مِنَ المَجْذُومِ كَمَا تَفِرُّ مِنَ الأَسَدِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 5707]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ ብለዋል፦ «የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፡
"የበሽታ (በራሱ) መተላለፍ የለም፣ ገድም የለም፣ የጉጉት ድምፅ (ተፅእኖም) የለም፣ የሰፈር ወር ገደቢስነትም የለም። ከአንበሳ እንደምትሸሽው ከቁምጥና ወረርሽኝም ሽሽ!"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 5707]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ነገሮች ባጠቃላይ በአላህ እጅ መሆናቸውንና በትእዛዙና በውሳኔው ካልሆነ በቀር ምንም ነገር እንደማይሆን ለመግለፅ አንዳንድ የድንቁርና ዘመን ጉዳዮችን አብራሩ። እነሱም:-
የመጀመሪያው: የድንቁርና ዘመን ሰዎች በሽታ በራሱ ይተላለፋል ብለው ያስቡ ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በሽታ በራሱ ከበሽተኛው ወደ ሌላው ይተላለፋል የሚለውን እምነት ከማመን ከለከሉ። በአጽናፈ ዓለሙ የሚያስተናብረው፣ በሽታን የሚያወርደውም የሚያነሳውም አላህ ብቻ ነው። ይህ ሁሉ በርሱ ፍላጎትና ውሳኔ ካልሆነ በቀር አይከሰትም።
ሁለተኛ: የድንቁርና ዘመን ሰዎች ለጉዞ ወይም ለንግድ የወጡ ጊዜ በራሪ ያበሩና ወደ ቀኝ አቅጣጫ ከበረረ ተስፋ ያደርጋሉ፤ ወደ ግራ አቅጣጫ ከበረረ ደግሞ እድለ ቢስነትን አምነው ይመለሱ ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከዚህ በበራሪ ገደቢስ ማመንን ከለከሉ። ከንቱ እምነት መሆኑንም ገለፁ።
ሶስተኛ: የድንቁርና ዘመን ሰዎች ጉጉት በአንድ ግቢ ላይ ካረፈ የዛ ግቢ ቤተሰብ መከራ ያጋጥመዋል ብለው ያምኑ ነበር። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከዚህ ገደቢስነት እምነት ከለከሉ።
አራተኛ: በሰፈር ወር ገደቢስነትን ከማመንም ከለከሉ። ይህ ወር በጨረቃ አቆጣጠር ሁለተኛው ወር ነው። ሰፈር በማለት የተፈለገው ከብቶችና ሰዎች ሆድ ውስጥ የሚገኝ ጥገኛ ትል ነው ተብሏል። ይህ ትልም ከቁምጥና በሽታ የበለጠ ይተላለፋል ብለው ይሞግታሉ ብለው የተረጎሙትም አሉ። ይህን እምነትም ውድቅ አደረጉ።
አምስተኛ: ከአንበሳ እንደምትርቀው በቁምጥና ከተያዘ ሰውም መራቅን አዘዙ። ይህም ለነፍስ ደህንነትን ከመፈለግ፣ ለጥንቃቄና አላህ ያዘዘውን ሰበብ ለማድረስ ያህል ነው። ቁምጥና (ሥጋ ደዌ): ሰውነትን የሚበላ የሆነ በሽታ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በአላህ ላይ መመካትና በርሱ ላይ መደገፍ ግዴታ መሆኑንና ሸሪዓዊ ሰበቦዎችን መፈፀምም እንደሚገባ እንረዳለን።
  2. በአላህ ፍርድና ውሳኔ ማመን ግዴታ እንደሆነና ሰበቦች በአላህ እጅ በመሆናቸው ተፅእኗቸው ተፈፃሚ የሚያደርገውም ይሁን ተፅእኗቸውን የሚያነሳው አሏህ ብቻ መሆኑን እንረዳለን።
  3. አንዳንድ ሰዎች እንደጥቁርና ቀይ ባሉ ቀለሞች ገደቢስነትን ማመናቸው ወይም በአንዳንድ ቁጥሮች፣ ስሞች፣ ግለሰቦችና በአካለ ስንኩላን ሰዎች ገደቢስነትን ማመናቸውን ውድቅ ያደርጋል።
  4. በቁምጥና ወረርሽኝና በመሰል ተላላፊ በሽታ ከተያዘ ሰው ከመቅረብ መከልከሉን እንረዳለን። ይህም መቀራረቡ በሽታው እንዲተላለፍ አሏህ ተለምዷዊ ሰበብ ያደረገው ስለሆነ ነው። ሰበቦች ራሳቸውን ችለው ተፅእኖ አይፈጥሩም። ነገር ግን አላህ ከፈለገ ኃይሏን ይነጥቃትና አንድም ተፅእኖ እንዳይኖራት ያደርጋል። ከፈለገ ደግሞ ተፅእኖዋን ባለባት ይተዋትና ተፅእኖዋን ታሳድራለች።
ተጨማሪ