عَنْ أَبٍي سَعِيدٍ الخُدْرِيَّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ:
أَنَّ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ جَلَسَ ذَاتَ يَوْمٍ عَلَى المِنْبَرِ وَجَلَسْنَا حَوْلَهُ، فَقَالَ: «إِنِّي مِمَّا أَخَافُ عَلَيْكُمْ مِنْ بَعْدِي، مَا يُفْتَحُ عَلَيْكُمْ مِنْ زَهْرَةِ الدُّنْيَا وَزِينَتِهَا» فَقَالَ رَجُلٌ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، أَوَيَأْتِي الخَيْرُ بِالشَّرِّ؟ فَسَكَتَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقِيلَ لَهُ: مَا شَأْنُكَ؟ تُكَلِّمُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ وَلاَ يُكَلِّمُكَ؟ فَرَأَيْنَا أَنَّهُ يُنْزَلُ عَلَيْهِ؟ قَالَ: فَمَسَحَ عَنْهُ الرُّحَضَاءَ، فَقَالَ: «أَيْنَ السَّائِلُ؟» وَكَأَنَّهُ حَمِدَهُ، فَقَالَ: «إِنَّهُ لاَ يَأْتِي الخَيْرُ بِالشَّرِّ، وَإِنَّ مِمَّا يُنْبِتُ الرَّبِيعُ يَقْتُلُ أَوْ يُلِمُّ، إِلَّا آكِلَةَ الخَضْرَاءِ، أَكَلَتْ حَتَّى إِذَا امْتَدَّتْ خَاصِرَتَاهَا اسْتَقْبَلَتْ عَيْنَ الشَّمْسِ، فَثَلَطَتْ وَبَالَتْ، وَرَتَعَتْ، وَإِنَّ هَذَا المَالَ خَضِرَةٌ حُلْوَةٌ، فَنِعْمَ صَاحِبُ المُسْلِمِ مَا أَعْطَى مِنْهُ المِسْكِينَ وَاليَتِيمَ وَابْنَ السَّبِيلِ - أَوْ كَمَا قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ - وَإِنَّهُ مَنْ يَأْخُذُهُ بِغَيْرِ حَقِّهِ، كَالَّذِي يَأْكُلُ وَلاَ يَشْبَعُ، وَيَكُونُ شَهِيدًا عَلَيْهِ يَوْمَ القِيَامَةِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1465]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው:
«ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ቀን ሚንበር ላይ ተቀመጡ እኛም በዙሪያቸው ተቀመጥን። እንዲህም አሉ" ከኔ በኋላ በናንተ ላይ ከምፈራላችሁ ነገሮች መካከል በናንተ ላይ የሚከፈትላችሁን የዱንያ ጌጥና ውበት ነው።" አንድ ሰውዬም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! መልካም ነገር መጥፎን ይዞብን ይመጣልን?" አላቸው። ነቢዩም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዝም አሉ። ሰሓቦችም ለርሱ "ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እያናገርካቸው ያላናገሩህ ምን ብትሆን ነው?" አሉት። በርሳቸው ላይ ወሕይ እየወረደ እንደሆነም ተመለከትን። ላባቸውንም ከላያቸው ላይ ጠረጉና ልክ እያመሰገኑት በሚመስል ሁኔታ "ጠያቂው የታለ?" አሉ። አክለውም "መልካም ነገር መጥፎ ነገርን ይዞ አይመጣም። በፀደይ ወቅት የሚበቅል ቡቃያ ግን ሊገድልም ወይ ለሞት ሊያቀርብም ይችላል። ጨፌውን የምትበላ እንስሳ ስትቀር። ሽንጧ እስኪለጠጥ ድረስ ትበላና ከዚያም ወደ ፀሐይ አቅጣጫ ዞራ ሰገራዋንና ሽንቷን ታወጣለች። ከዚያም ድጋሚ ትግጣለች። ይህ ገንዘብም ጣፋጭና ለምለም ነው። ለሚስኪኖች፣ ለየቲሞችና ለመንገደኞች የሰጠ ሙስሊም ሰው ምነኛ አማረለት!" ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንደዛ ነገር አሉ። "ይህን ገንዘብ ያለአግባብ የሚይዘው ሰው በልቶ እንደማይጠግብ ነው። በትንሳኤ ቀንም በርሱ ላይ ምስክር ይሆንበታል።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1465]
አንድ ቀን ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ባልደረቦቻቸውን ለማናገር ሚንበር ላይ ተቀመጡና እንዲህ አሉ:
ከኔ በኋላ በናንተ ላይ እጅግ አብዝቼ የምፈራላችሁ ነገር ቢኖር ለጥቂት ጊዜ የሚቆይ ከመሆኑም ጋር ለናንተ የሚከፈትላችሁን የምድር በረከት፣ የዱንያ ጌጥና ውበት፣ በውስጧ ያለውን የልብስ፣ የአዝርዕትና ሌሎችም ሰዎች በውበቱ የሚፎክሩበት የመጣቀሚያ አይነቶችን ነው።
አንድ ሰውዬ እንዲህ አለ: የዱንያ ውበት የአላህ ፀጋ ነው። ይህ ፀጋ ታዲያ ወደ ቅጣትና መዐትነት ይለወጣል ማለት ነውን?
ሰዎች የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዝምታ ሲመለከቱ አስቆጥቷቸዋል ብለው በማሰብ ጠያቂውን ወቀሱት።
በነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ላይ ወሕይ እየወረደ እንደነበር ግልፅ ሆነላቸው። ቀጥለውም ላባቸውን ከግንባራቸው ላይ እየጠረጉ ጠያቂው የት አለ? አሉ።
እርሱም "እኔ ነኝ!" አለ።
አላህን አመሰግነው በርሱም ላይ ካወደሱ በኃላ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ አሉ: "ትክክለኛ መልካም ነገር መልካሙን እንጂ ሌላ ነገር ይዞ አይመጣም። ነገር ግን ይህቺ የዱንያ ውበት ወደ ፈተና፣ እሽቅድድም፣ ወደ መጪው አለም ሙሉ ለሙሉ ከመዞር ስለምታጠምድ ጥርት ባለ መልኩ መልካም አይደለችም። ቀጥለው እንዲህ በማለት ለዚህ ምሳሌን ጠቀሱ "የፀደይ ቡቃያና አትክልት እንስሶች ለመጋጥ የሚወዱት ስለሆነ አብዝተው በመብላታቸው በቁንጣን ይገላቸዋል፤ ወይም ወደ ሞት ያቀርባቸዋል። ይህ ግን የሆዷ አንድ ጎን እስኪሞላ አትክልቱን ግጣ ቀጥላ ወደ ፀሃይ ዞራ ከሆዷ ቀጭን ሰገራዋን አውጥታ ወይም ሸንታ ሆዷ የገባውን መልሳ አውጥታ አመንዥካ ድጋሚ የምትውጥ ከዚያም ተመልሳ የምትግጥ እንስሳን አይገድላትም። አሉ።
ይህ ገንዘብም እንደ ጣፋጭ አትክልትና ቡቃያ ነው። በሐላል መንገድ አግኝቶት በሚያስፈልገው ያህልና በቂውን በሚያገኝበት ብቻ በጥቂት ገንዘብ ላይ የተብቃቃ ሲቀር ከበዛ ይገድላል ወይም ለመግደል ይቀርባል። የሚያስፈልገውን ብቻ ከሆነ የሚጠቀመው አይጎዳውም። ለሚስኪኖች፣ ለየቲሞችና ለመንገደኞች የሚሰጥ ሙስሊም ሰው ምንኛ ያማረ ነው! ገንዘብን በአግባቡ የሚይዝ ይባረክለታል። ያለአግባብ የሚይዘው ደግሞ የርሱ ምሳሌ እየበላ እንደማይጠግብ ሰው ምሳሌ ነው። በርሱ ላይም የትንሳኤ ቀን ይመሰከርበታል።