عَنْ أَبِي مُوسَى رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَثَلُ الَّذِي يَذْكُرُ رَبَّهُ وَالَّذِي لاَ يَذْكُرُ رَبَّهُ، مَثَلُ الحَيِّ وَالمَيِّتِ»، ولفظ مسلم: «مَثَلُ الْبَيْتِ الَّذِي يُذْكَرُ اللهُ فِيهِ، وَالْبَيْتِ الَّذِي لَا يُذْكَرُ اللهُ فِيهِ، مَثَلُ الْحَيِّ وَالْمَيِّتِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6407]
المزيــد ...
ከአቡሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ጌታውን የሚያወሳና የማያወሳ ሰው ምሳሌ እንደ ህያውና እንደ ሞተ ሰው ምሳሌ ነው።"» በሙስሊም ዘገባ ደሞ "በውስጡ አላህ የሚወሳበት ቤትና አላህ የማይወሳበት ቤት ምሳሌ እንደ ህያውና እንደሞተ ሰው ምሳሌ ነው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6407]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህን በሚያወሳና በማያወሳ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት ከጥቅሙና ማንነቱ ከማማሩ አንፃር የነርሱ ምሳሌን በህይወት ባለና በሞተ ሰው ምሳሌ ገለፁ። ጌታውን የሚያወሳ ሰው ምሳሌ ውጫዊ ማንነቱ በህይወት ብርሃን፣ ውስጣዊ ማንነቱ ደግሞ በእውቀት ብርሃን እንደተዋበ ሰው ነው። ጥሩ ነገር ያለውም እዚህ ላይ ነው። አላህን የማያወሳ ሰው ምሳሌ ደግሞ ውጫዊ ማንነቱ ከውበት እንደተራቆተ ውስጣዊ ማንነቱ ደግሞ በጥመት እንደተሞላ ሙት ሰው ነው ምሳሌው። ከርሱም ጥሩ ነገር አይገኝም።
ልክ እንደዚሁ ቤትም የሚኖሩበት ሰዎች አላህን የሚያወሱ ከሆኑ በህያውነት ያለበለዚያ ደግሞ ነዋሪዎቹ አላህን ከማውሳት የተራቆቱ ስለሆኑ በሙታን ይመሰላል። ህያውነትና ሙታንነት የሚለው ባህሪ ለቤት ከሆነ የዋለው የሚፈለግበት ቤቱ ውስጥ የሚኖሩትን ነው።