+ -

عَنْ أَبِي مُسْلِمٍ الْخَوْلَانِيِّ، قَالَ: حَدَّثَنِي الْحَبِيبُ الْأَمِينُ، أَمَّا هُوَ فَحَبِيبٌ إِلَيَّ، وَأَمَّا هُوَ عِنْدِي فَأَمِينٌ، عَوْفُ بْنُ مَالِكٍ الْأَشْجَعِيُّ رضي الله عنه قَالَ:
كُنَّا عِنْدَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، تِسْعَةً أَوْ ثَمَانِيَةً أَوْ سَبْعَةً، فَقَالَ: «أَلَا تُبَايِعُونَ رَسُولَ اللهِ؟» وَكُنَّا حَدِيثَ عَهْدٍ بِبَيْعَةٍ، فَقُلْنَا: قَدْ بَايَعْنَاكَ يَا رَسُولَ اللهِ، ثُمَّ قَالَ: «أَلَا تُبَايِعُونَ رَسُولَ اللهِ؟» فَقُلْنَا: قَدْ بَايَعْنَاكَ يَا رَسُولَ اللهِ، ثُمَّ قَالَ: «أَلَا تُبَايِعُونَ رَسُولَ اللهِ؟» قَالَ: فَبَسَطْنَا أَيْدِيَنَا وَقُلْنَا: قَدْ بَايَعْنَاكَ يَا رَسُولَ اللهِ، فَعَلَامَ نُبَايِعُكَ؟ قَالَ: «عَلَى أَنْ تَعْبُدُوا اللهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا، وَالصَّلَوَاتِ الْخَمْسِ، وَتُطِيعُوا -وَأَسَرَّ كَلِمَةً خَفِيَّةً- وَلَا تَسْأَلُوا النَّاسَ شَيْئًا» فَلَقَدْ رَأَيْتُ بَعْضَ أُولَئِكَ النَّفَرِ يَسْقُطُ سَوْطُ أَحَدِهِمْ، فَمَا يَسْأَلُ أَحَدًا يُنَاوِلُهُ إِيَّاهُ.

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1043]
المزيــد ...

ከአቡ ሙስሊም አልኸውላኒ እንደተላለፈው እንዲህ አሉ "ተወዳጁና ታማኙ ሰው ይህንን ሐዲሥ ነገረኝ። እርሱ እኔ ዘንድ ተወዳጅነትም ታማኝነትም አለው። ይሀውም ዐውፍ ቢን ማሊክ አልአሽጀዒይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ:
'የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ ዘጠኝ ወይም ስምንት ወይም ሰባት ሆነን ሳለ እንዲህ አሉን ‹ለአላህ መልክተኛ ቃል አትጋቡምን?› ቃልኪዳን ከተጋባናቸው ቅርብ ጊዜ ነበርንና ‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርግጥ ቃልኪዳን ተጋብተኖታል'ኮ› አልናቸው። ቀጥለውም ‹ለአላህ መልክተኛ ቃል አትጋቡምን?› አሉ። እኛም ‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርግጥ ቃልኪዳን ተጋብተኖታል'ኮ› አልናቸው። ቀጥለውም ‹ለአላህ መልክተኛ ቃል አትጋቡምን?› አሉ። የዛኔ እጃችንን (ቃልኪዳን ለመጋባት) ዘርግተን ‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርግጥ ቃልኪዳን ተጋብተኖታል። በምን ጉዳይ ላይ ነው ቃልኪዳን የምንጋባዎት?› አልናቸው። እርሳቸውም ‹አላህን በርሱ አንዳችም ሳታጋሩ በመገዛት፣ በአምስቱ ሶላቶች ላይ፣ በታዛዥነት፣ (ዝግ ባለ ድምፅ የተወሰኑ ቃላቶችን ተናገሩ።) ሰዎችን አንዳችም ነገር ባለመጠየቅ።› አሉን።' በርግጥም ከነዚህ (ቃልኪዳን ከተጋቡት ውስጥ) የተወሰኑትን የአንዳቸው አለንጋ ወድቆ አንድንም ሰው እንዲያቀብለው የማይጠይቅ ሆኖ ተመልክቻለሁ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1043]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከተወሰኑ ሶሐቦች የሆኑ ጉዳዮችን አጥብቆ ለመያዝ ቃልኪዳን እንዲጋቡዋቸው ሶስት ጊዜ ፈለጉ።
የመጀመሪያው: አላህን ትእዛዙን በመተግበር ክልከላውን በመራቅ በብቸኝነት ማምለክና በርሱ ላይ አንዳችንም ላያጋሩ ነው።
ሁለተኛው: አምስቱን ግዴታ ሶላቶች በቀንና በምሽት ቀጥ አድርጎ መስገድ ነው።
ሶስተኛው: የሙስሊሞችን ጉዳይ እንዲመራ ለተሾመ ሰው በመልካም ጉዳዮች ሰምቶ መታዘዝ ነው።
አራተኛው: ሁሉንም ጉዳያቸውን ወደ አላህ በማስጠጋት ሰዎችን አንዳችም ነገር አለመጠየቅ ነው። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን ሲናገሩ ድምፃቸውን ዝግ አደረጉ።
ሐዲሡን ያስተላለፈው፦ "ከነዚህ ሶሐቦች የተወሰኑትን የአንዳቸው አለንጋ ሲወድቅ እንኳ ወርዶ በራሱ ያነሳዋል እንጂ አንድም ሰው አለንጋውን እንዲያቀብለው የማይጠይቅ ሆነው ተመልክቻቸዋለሁ።" ብሎ እስኪገልፃቸው ድረስ ሶሐቦቹ (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና የተጋቡትን ቃልኪዳን ተግባራዊ አድርገውታል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية Malagasisht Oromisht Kannadisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሰዎችን ከመለመን መታቀብ ላይ መነሳሳቱ፤ ሰውን መለመን ተብሎ ከሚታሰብ ነገር ሁሉ መጥራራት፤ በቀላል ነገር ላይ እንኳ ሳይቀር ከሰዎች መብቃቃት እንደሚገባ እንረዳለን።
  2. የተከለከለው ልመና፦ ከዱንያዊ ጉዳዮች ጋር የተያያዙ ልመናዎችን ነው እንጂ ስለ እውቀትና ስለሃይማኖታዊ ጉዳይ መጠየቅን አያካትትም።
ተጨማሪ