عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«مَا مِنْ قَوْمٍ يَقُومُونَ مِنْ مَجْلِسٍ لَا يَذْكُرُونَ اللَّهَ فِيهِ إِلَّا قَامُوا عَنْ مِثْلِ جِيفَةِ حِمَارٍ، وَكَانَ لَهُمْ حَسْرَةً».
[صحيح] - [رواه أبو داود] - [سنن أبي داود: 4855]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል:
"ሰዎች በውስጧ አላህን ያላወሱበትን መሰባሰብን (ጨርሰው) አይነሱም። የአህያ ሬሳ (በልተው) እንደሚሄዱ እና (በስብሰባው አላህን ባለማውሳታቸው) በእነርሱ ላይ ጸጸት (ቁጭትን) ቢሆንባቸው እንጂ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 4855]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በግማትና ቀፋፊነት በአህያ ጥንብ ላይ እንደተሰባበሱ ሰዎች አምሳያ ሆነው የሚነሱ እንጂ አንድ ስፍራ ላይ ተቀምጠው ከዚያም በዛ ስፍራ አላህን ሳያወሱበት የሚነሱ ሰዎች የሉም። ይህም አላህን ከማውሳት በወሬ ስለተጠመዱ ነው። የትንሳኤ ቀንም በዚህ አቀማመጣቸው ሰበብ በነርሱ ላይ ቁጭት፣ ጉድለትና ፀፀት እንደማይለቃቸው ተናገሩ።