+ -

عَن أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ: قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«يَأْتِي الشَّيْطَانُ أَحَدَكُمْ فَيَقُولُ: مَنْ خَلَقَ كَذَا؟ مَنْ خَلَقَ كَذَا؟ حَتَّى يَقُولَ: مَنْ خَلَقَ رَبَّكَ؟ فَإِذَا بَلَغَهُ فَلْيَسْتَعِذْ بِاللهِ وَلْيَنْتَهِ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3276]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው፦ የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦
"ሰይጣን አንዳችሁ ዘንድ በመምጣት "ይህን የፈጠረው ማነው? ይህንንስ የፈጠረው?" እያለ ይጠይቃችኋል "ጌታህንስ የፈጠረው ማነው?" ብሎ እስኪጠይቃችሁ ድረስ ይደርሳል፤ ይህ ጥያቄ የደረሰው ጊዜ በአላህ ይጠበቅም ይከልከልም።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3276]

ትንታኔ

የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሰይጣን አማኞችን ለመጎትጎት ለሚያቀርባቸው ጥያቄዎች ፍቱን መድኃኒት ተናገሩ። "ይህን ማን ፈጠረው? ይህንንስ ማን ፈጠረው? ሰማይን ማን ነው የፈጠረው? ምድርንስ ማን ነው የፈጠረው?" በማለት ሰይጣን ጥያቄ ያቀርብልናል። አማኙም በእምነቱም ፣ በተፈጥሮውም፣ በአይምሮውም ተጠቅሞ "አላህ" በማለት ይመልስለታል። ሰይጣን ግን በዚህ የጉትጎታ ወሰን ላይ ከመቆም ይልቅ "ጌታህን ማን ፈጠረው?" ወደሚል የጉትጎታ ደረጃ ይሸጋገራል። በዚህ ጊዜ አንድ አማኝ ይህንን ጉትጎታ በሦስት ነገሮች ይከላከላል፦
በአላህ በማመን
ከሰይጣን በአላህ በመጠበቅ
ከጉትጎታው ጋር አብሮ መቀጠልን በማቆም

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht اليونانية الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የሰይጣንን ጉትጎታና ውልታ ችላ ማለት፤ ስለ እሱ ማሰብ እንደማይገባ እና ይህን ለማስወገድ ወደ አላህ መጠጋት የሚገባ መሆኑን።
  2. ሁሉም በሰው ልጅ ቀልብ ውስጥ የሚከሰት ሸሪዐን ተፃራሪ የሆነ ጉትጎታ ከሰይጣን መሆኑን ፤
  3. በአላህ ህልውና ጉዳይ ማስተንተን መከልከሉና ስለፍጡራኑና አንቀፆቹ ማስተንተን መበረታታቱን ተረድተናል።
ተጨማሪ