عن ابن عباس رضي الله عنهما قال:
جاءَ رجُلُ إلى النبي صلى الله عليه وسلم فقال: يا رسولَ اللهِ، إن أحدنا يجدُ في نفسِهِ -يُعرِّضُ بالشَّيءِ- لأَن يكونَ حُمَمَةً أحَبُّ إليه من أن يتكلَّم بِهِ، فقال: «اللهُ أكبرُ، اللهُ أكبرُ، الحمدُ لله الذي ردَّ كيدَه إلى الوسوسَةِ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والنسائي في الكبرى] - [سنن أبي داود: 5112]
المزيــد ...
ኢብኑ ዐባስ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ ብለዋል፦
አንድ ሰው ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት እንዲህ አለ፦ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን እሱን ከመናገር ይልቅ አመድ መሆን የሚያስደስተውን ነገር በነፍሱ ውስጥ ይሰማዋል።" እርሳቸውም፦ "አላሁ አክበር አላሁ አክበር የሰይጣንን ተንኮል ወደ ጉትጎታ የመለሰው አላህ ምስጋና ይገባው።" አሉ።
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድና ነሳኢ በኩብራ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 5112]
አንድ ሰው ወደ ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን በመምጣት እንዲህ አለ፦ የአላህ መልክተኛ ሆይ! አንዳችን በነፍሱ ውስጥ የሚመላለስ ነገርን በውስጡ ይሰማዋል። ነገር ግን እሱን ከመናገር ይልቅ አመድ መሆን እስኪመኝ ድረስ እሱን መናገር ይከብደዋል። መልክተኛውም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ሁለት ጊዜ ተክቢር በማሰማት የሰይጣንን ተንኮል ወደ ጉትጎታ ብቻ በመመለሱ አላህን አመሰገኑ።