عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ قَالَ: سُبْحَانَ اللهِ وَبِحَمْدِهِ، فِي يَوْمٍ مِائَةَ مَرَّةٍ، حُطَّتْ خَطَايَاهُ وَإِنْ كَانَتْ مِثْلَ زَبَدِ الْبَحْرِ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ሱብሓነላሂ ወቢሐምዲሂ "ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።" ያለ ሰው (የወንጀሉ ብዛት) የባህር ዓረፋ አምሳያ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይታበስለታል።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ "ሱብሓነሏሂ ወቢሐምዲሂ" (ጥራት ምስጋና ለአላህ ይገባው።) ያለ ሰው ባህር በሚናወጥ ወቅት ከላዩ እንደሚንጣለለው ነጭ አረፋ አምሳያ ወንጀሉ የበዛ ቢሆን እንኳ ወንጀሉ ይማራል ይታበሳል ብለው ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እየተናገሩ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ይህን ምንዳ የሚያገኘው በቀን ውስጥ አከታትሎም ይሁን በተለያየ ጊዜ እነዚህን ቃላት ያለ ሰው ነው።
  2. ተስቢሕ ማለት: - አላህን ከጉድለት ማጥራት ሲሆን ፤ ሐምድ ማለት ደግሞ አላህን ከመውደድና ከማላቅ ጋር በምሉዕነት መግለፅ ነው።
  3. በሐዲሡ ወንጀልን ማስማር ከሚለው የተፈለገበት ትናንሽ ወንጀሎችን ብቻ ነው። ትላልቅ ወንጀሎች ግን የግድ ተውበት ያስፈልጋቸዋል።