عن أبي أيوب رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«مَنْ قَالَ: لَا إِلَهَ إِلَّا اللهُ وَحْدَهُ لَا شَرِيكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ، عَشْرَ مِرَارٍ كَانَ كَمَنْ أَعْتَقَ أَرْبَعَةَ أَنْفُسٍ مِنْ وَلَدِ إِسْمَاعِيلَ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአቡ አዩብ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
"አስር ጊዜ 'ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር' ያለ ሰው ከኢስማዒል ዘሮች የሆኑ አራት ነፍሶችን ነፃ እንዳወጣ ይቆጠርለታል።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

በዚህ ሐዲሥ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደሚነግሩን ይህንን ውዳሴ ያለ፦ "ላ ኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ ፤ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ትርጉሙም: ከአላህ ውጪ በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም፤ ብቸኛና ለሱ አጋር የለውም፤ ጥራት የተገባው አላህ በምሉዕ ንግስና የተለየ ነው፤ ከሱ ውጪ ያሉት የማይገባቸውን ውዳሴና ሙገሳ ከውዴታና ልቅና ጋር በብቸኝነት የተገባው ነው ፤ እርሱም አንዳችም የማያቅተው ቻይ ነው። ይህንን ታላቅ ውዳሴም በቀን አስር ጊዜ የደጋገመም ሰው በነርሱ ላይ የአላህ ሶላትና ሰላም ይስፈንና የኢብራሂም ልጅ ከሆኑት ከኢስማዒል ዘሮች አራት ባሮችን ከባርነት ነፃ እንዳወጣ ሰው ምንዳ አምሳያ ለርሱ ይኖረዋል። የኢስማዒል ዐለይሂ ሰላም ዘሮች የተለዩትም እነርሱ ከሌሎች የላቁ ስለሆኑ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የዚህ ውዳሴ ትሩፋት አላህን በተመላኪነት፣ በንግስና፣ በምስጋናና በተሟላ ችሎታ መነጠልን ያካተተ ነው።
  2. ይህንን ውዳሴ አከታትሎም ሆነ በተለያየ ቆይታ ያለ ሰው የዚህን ውዳሴ ምንዳ እንደሚያገኝ እንረዳለን።