+ -

عن عائشةَ أُمِّ المُؤْمِنينَ رضي الله عنها:
أن النبي صلى الله عليه وسلم كان لا يَدع أربعا قَبل الظهر وركعتين قبل الغَدَاة.

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 1182]
المزيــد ...

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው፦
"ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከዝሁር በፊት አራት ረከዓና ከፈጅር በፊት ሁለት ረከዓ አይተዉም ነበር።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1182]

ትንታኔ

እናታችን ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እርሷ ቤት ውስጥ በሱና ሶላቶች ይዘወትሩ እንደነበር ተናገረች። እነዚያ ሱና ሶላቶችም ከዝሁር ሶላት በፊት በሁለት ማሰላመት አራት ረከዓ ሶላትና ከፈጅር ሶላት በፊት ደግሞ ሁለት ረከዓ ሶላት ናቸው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከዝሁር ሶላት በፊት አራት ረከዓ ሶላት ላይና ከፈጅር ሶላት በፊት ደግሞ ሁለት ረከዓ ሶላት ላይ መጠባበቅ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. በላጩ ሱና ሶላቶች ቤት ውስጥ መሰገዳቸው ነው። ስለዚህ ጉዳይ የተናገረችው ዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ‐ መሆኗም ከዛ አንፃር ነው።