+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رضي الله عنه قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«إِذَا شَكَّ أَحَدُكُمْ فِي صَلَاتِهِ، فَلَمْ يَدْرِ كَمْ صَلَّى ثَلَاثًا أَمْ أَرْبَعًا، فَلْيَطْرَحِ الشَّكَّ، وَلْيَبْنِ عَلَى مَا اسْتَيْقَنَ، ثُمَّ يَسْجُدُ سَجْدَتَيْنِ قَبْلَ أَنْ يُسَلِّمَ، فَإِنْ كَانَ صَلَّى خَمْسًا شَفَعْنَ لَهُ صَلَاتَهُ، وَإِنْ كَانَ صَلَّى إِتْمَامًا لِأَرْبَعٍ كَانَتَا تَرْغِيمًا لِلشَّيْطَانِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 571]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ብለዋል፦
"አንዳችሁ ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ ጊዜ ሶስት ይሁን አራት ስንት እንደሰገደ ካላወቀ ጥርጣሬውን ይጣልና እርግጠኛ በሆነበት ላይ ይገንባ። ከዛም ከማሰላመቱ በፊት ሁለት ሱጁዶችን ይውረድ። አምስት ከሰገደ ሁለቱ ሱጁዶች ሶላቱን ጥንድ ያደርጉለታል። አራት ሞልቶ ከሰገደ ደግሞ ሱጁዶቹ ሰይጣንን ማዋረጃ ይሆኑለታል።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 571]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድ ሰጋጅ ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ ጊዜና ሶስት ይሁን አራት ስንት እንደሰገደ ካላወቀ ምን ማድረግ እንዳለበት ገለፁ። ሶስተኛው ስለሆነ የተረጋገጠው አጠራጣሪውን የረከዓ ብዛት (አራትን) ሳይቆጥር አራተኛውን ረከዓ ይሰግዳል። ከዚያም ከማሰላመቱ በፊት ሁለት ሱጁዶችን ይወርዳል።
የሰገደው እውነትም አራት ከነበር አንድ ረከዓ በመጨመሩ አምስተኛ ይሆናል። ሁለቱ የመርሳት ሱጁዶችም እንደ አንድ ረከዓ ይሆኑለትና ስለዚህ የረከዓው ብዛት ሙሉ እንጂ ጎዶሎ አይሆንም። ጭማሪዋ ረከዓ እውነትም አራተኛ ከሆነች ደግሞ በርሱ ላይ ያለበትን ግዴታ ሳይጨምርና ሳይቀንስ ተወጥቷል።
ሁለቱ ሱጁዶችም ሰይጣንን ማዋረጃና ማራቂያ እንዲሁም ፍላጎቱን ሳያሳካ ባዶ እጁን መመለሻ ይሆናሉ። ምክንያቱም ሶላቱ ውስጥ አወሳስቦበት እንዲበላሽበት ተጋረጠበት፤ ሰጋጁ የአደም ልጅም ‐ ለአደም ሱጁድ ውረድ የሚለውን የአላህን ትእዛዝ ባለመፈፀም ኢብሊስ ያመፀበት የሆነውን ‐ የሱጁድን ትእዛዝ በመፈፀሙ ሶላቱ ሞላለት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الدرية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሰጋጅ የሆነ ሰው ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ ጊዜና እርሱ ዘንድ አንዱ ሚዛን ካልደፋ ጥርጣሬውን ይጥልና እርግጠኛ በሆነበት ነገር ላይ ይሰራል። ይሀውም አነስተኛ የሆነውን ነው (የሰገድኩት ሶስት ረከዓ ነው ወይስ አራት ብሎ ከተጠራጠረ ሶስት የሚለውን ይወስዳል)። ሶላቱን አሟልቶ ይሰግድና ከማሰላመቱ በፊት የመርሳት ሱጁድን ይወርዳል፤ ከዚያም ያሰላምታል።
  2. እነዚህ ሁለት ሱጁዶች ሶላትን መጠገኛ መንገድና ሰይጣንን ከፍላጎቱ የተዋረደ፣ የራቀና ባዶውን መመለሻ ናቸው።
  3. ሐዲሡ ውስጥ የተጠቀሰው ጥርጣሬ ሚዛን ያልደፋውን ጥርጣሬ ነው እንጂ ጥርጣሬው ሚዛን የሚደፋ ከሆነ ግን ሚዛን በሚደፋው ነው የሚሰራው።
  4. ሸሪዓዊን ትእዛዝ በመፈፀም ወስዋስን መዋጋትና መከላከል ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
ተጨማሪ