+ -

«‌لَيَبْلُغَنَّ ‌هَذَا الأَمْرُ مَا بَلَغَ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ، وَلَا يَتْرُكُ اللهُ بَيْتَ مَدَرٍ وَلَا وَبَرٍ إِلَّا أَدْخَلَهُ اللهُ هَذَا الدِّينَ*، بِعِزِّ عَزِيزٍ أَوْ بِذُلِّ ذَلِيلٍ، عِزًّا يُعِزُّ اللهُ بِهِ الإِسْلَامَ، وَذُلًّا يُذِلُّ اللهُ بِهِ الكُفْرَ»* وَكَانَ تَمِيمٌ الدَّارِيُّ يَقُولُ: قَدْ عَرَفْتُ ذَلِكَ فِي أَهْلِ بَيْتِي، لَقَدْ أَصَابَ مَنْ أَسْلَمَ مِنْهُمُ الْخَيْرُ وَالشَّرَفُ وَالْعِزُّ، وَلَقَدْ أَصَابَ مَنْ كَانَ مِنْهُمْ كَافِرًا الذُّلُّ وَالصَّغَارُ وَالْجِزْيَةُ.
[صحيح] - [رواه أحمد]
المزيــد ...

ከተሚም አድዳሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
"የዚህ ሃይማኖት ጉዳይ ቀንና ምሽት የደረሰበት ስፍራ ሁሉ ይደርሳል። አላህ፤ በሀያሉ ሀይልም ይሁን በውርደታሞች ውርደት ይህንን ሃይማኖት እያንዳንዱ የግንብ (የከተማ) ቤት ውስጥም ይሁን የሳር ቤት (የገጠር ቤት) ውስጥ ሳያስገባው አይቀርም። ወይ አላህ በርሱ ኢስላምን የበላይ በሚያደርግበት ሀይል አልያም አላህ በርሱ ክህደትን በሚያዋርድበት ውርደት (ኢስላም የበላይነቱን ይጎናፀፋል)።"» ተሚም አድዳሪም እንዲህ ይል ነበር "ይህንንም በወገኖቼ አወቅኩት። ከወገኖቼ የሰለሙት መልካምን፣ ልቅናና ክብርን አገኙ። ከወገኖቼ መካከል የካዱትንም ውርደት፣ የበታችነትና ግብር አገኛቸው።"

ሶሒሕ ነው። - አሕመድ ዘግበውታል።

ትንታኔ

የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህ ሃይማኖት የምድርን አጠቃላይ ክፍል እንደሚያዳርስ፣ ማንኛውም ሌሊትና ቀን የተፈራረቀበት ስፍራ ሁሉ ይህ እምነት እንደሚደርሰው ተናገሩ። አላህ አንድንም ከተማና መንደር ሆነ አልያም ገጠርና በረሃ ይህ እምነት እንዲገባበት ሳያደርግ እንደማይተወው ተናገሩ። ይህንን ሃይማኖት ተቀብሎ ያመነበት ሰው በእስልምና ልቅና የበላይ ይሆናል። ይህንን ሃይማኖት አልቀበል ያለና የካደበት ደግሞ የተዋረደና የበታች ይሆናል።
ቀጥሎ ሶሐባው ተሚም አድዳሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ይህን የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) የተናገሩበትን ጉዳይ ልዩ በሆነ መልኩ በቤተሰቦቹ ውስጥ እንዳስተዋለው ተናገረ። ከነርሱ መካከል የሰለሙት መልካምን፣ ክብርና ልቅናን ያገኙ ሲሆን ከነርሱ መካከል የካዱት ደግሞ ለሙስሊሞች ከሚሰጡት ገንዘብ ተጨማሪ ውርደትና የበታቸኝነትን አግኝቷቸዋል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ السويدية القيرقيزية اليوروبا الدرية الصومالية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሙስሊሞች ሃይማኖታቸው በምድር ክፍል ባጠቃላይ መሰራጨቱ እንደማይቀር ተነግሯቸው መበሰራቸው።
  2. ልቅና የእስልምናና የሙስሊሞች ሲሆን ውርደት ደግሞ የክህደትና የከሀዲያን ነው።
  3. እዚህ ሐዲሥ ውስጥ ከነቢይነት ምልክቶች መካከል አንዱ አለ። ይህም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንደተናገሩት በመከሰቱ ነው።