عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا: أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«إِنَّ أَحَدَكُمْ إِذَا مَاتَ عُرِضَ عَلَيْهِ مَقْعَدُهُ بِالْغَدَاةِ وَالعَشِيِّ، إِنْ كَانَ مِنْ أَهْلِ الجَنَّةِ فَمِنْ أَهْلِ الجَنَّةِ، وَإِنْ كَانَ مِنْ أَهْلِ النَّارِ فَمِنْ أَهْلِ النَّارِ، فَيُقَالُ: هَذَا مَقْعَدُكَ حَتَّى يَبْعَثَكَ اللَّهُ يَوْمَ القِيَامَةِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1379]
المزيــد ...
ከዐብደላህ ቢን ዑመር ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
«አንዳችሁ የሞተ ጊዜ ለርሱ ጧትም ማታም ማረፊያው ይቀርብለታል። የጀነት ነዋሪ ከሆነ የጀነት ነዋሪዎች (ማረፊያ) የእሳት ነዋሪ ከሆነም የእሳት ነዋሪዎች (ማረፊያ እየቀረበለት) "አላህ የትንሳኤ ቀን እስኪቀሰቅስህ ድረስ ይህ ነው ማረፊያህ!" ይባላልም።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1379]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- አንድ ባሪያ የሞተ ጊዜ የቀኑ መጀመሪያና መጨረሻ ላይ ጀነት ውስጥ ወይም እሳት ውስጥ የሚገኘውን ልዩ ማረፊያውና ስፍራው ይቀርብለታል። የጀነት ነዋሪ ከሆነ የጀነት ስፍራው፤ የእሳት ነዋሪ ከሆነም የእሳት ስፍራው ይቀርብለታል። እንዲህም ይባላል: "ይህ የትንሳኤ ቀን የምትቀሰቀስበት ማረፊያህ ነው።" ይህም ለአማኞች ማስደሰቻ ሲሆን ለከሃዲያን ደሞ መቀጣጫ የሆነ ንግግር ነው።