عَن هَانِئ مَوْلَى عُثْمَانَ رَضيَ اللهُ عنهُ قَالَ: كَانَ عُثْمَانُ إِذَا وَقَفَ عَلَى قَبْرٍ بَكَى حَتَّى يَبُلَّ لِحْيَتَهُ، فَقِيلَ لَهُ: تُذْكَرُ الْجَنَّةُ وَالنَّارُ فَلَا تَبْكِي، وَتَبْكِي مِنْ هَذَا؟ فَقَالَ: إِنَّ رَسُولَ اللهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ:
«إِنَّ الْقَبْرَ أَوَّلُ مَنْزِلٍ مِنْ مَنَازِلِ الْآخِرَةِ، فَإِنْ نَجَا مِنْهُ فَمَا بَعْدَهُ أَيْسَرُ مِنْهُ، وَإِنْ لَمْ يَنْجُ مِنْهُ فَمَا بَعْدَهُ أَشَدُّ مِنْهُ».
[حسن] - [رواه الترمذي وابن ماجه] - [سنن الترمذي: 2308]
المزيــد ...
የዑሥማን (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ነፃ የወጣ ባሪያቸው ከሆነው ከሃኒእ እንደተላለፈው እንዲህ አለ: «ዑሥማን ቀብር ላይ የቆመ ጊዜ ፂሙ እስኪረጥብ ድረስ ያለቅስ ነበር። ለርሱም "ጀነትና እሳት በሚወሱ ጊዜ አታለቅስም። በዚህ ግን ታለቅሳለህን?" ተባለ። እርሱም እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ቀብር የመጪው ዓለም የመጀመሪያው ማረፊያ ነው። ከቀብር (ቅጣት) ከዳነ ከቀብር በኋላ ያለው ከርሱ የበለጠ ቀላል ነው። ከቀብር (ቅጣት) ካልዳነ ከቀብር በኋላ ያለው ቅጣት ከርሱ የበረታ ነው።"»
[ሐሰን ነው።] - [ቲርሚዚና ኢብኑማጀህ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2308]
የአማኞች መሪ ዑሥማን ቢን ዓፋን (ረዺየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ቀብር ላይ የቆሙ ጊዜ በእንባቸው ፂማቸው እስኪረጥብ ድረስ ያለቅሱ ነበርና እንዲህ ተባሉ: ጀነትና እሳት ሲወሱ ጀነትን ከመናፈቅ ወይም እሳትን በመፍራት ምክንያት ሳታለቅስ ቀብር ላይ ሲሆን ታለቅሳለህ? እርሳቸውም "ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ቀብር ከመጪው አለም ማረፊያዎች መካከል የመጀመሪያው ማረፊያ እንደሆነ ተናግረዋል። ከቀብር ቅጣት ከዳነና ከተገላገለ ከርሱ በኋላ ያለው ማረፊያ ቀላል ነው። ከቀብር ቅጣት ካልዳነ ደግሞ ከርሱ በኋላ ያለው ቅጣት ከርሱ የበረታ ነው።" ብለዋል አለ።