عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«الحَسَن والحُسَيْن سَيِّدا شَباب أهْل الجنة».
[صحيح] - [رواه الترمذي وأحمد] - [سنن الترمذي: 3768]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
"ሐሰንና ሑሰይን የጀነት ነዋሪ ወጣቶች አለቆች ናቸው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3768]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የርሳቸው ልጅ ልጆች የሆኑትና የዐሊይ ቢን አቢ ጧሊብና የፋጢማ ቢንት ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ልጆች የሆኑት ሐሰንና ሑሰይን ወጣት ሆኖ ሞቶ በአላህ ችሮታ ጀነት ለገባ ሰው ሁሉ አለቃ እንደሆኑ ወይም ከነቢያትና ከነቢዩ ቅን ምትክ መሪዎች ውጪ ላሉ የጀነት ወጣት ነዋሪዎች በሙሉ አለቃ እንደሆኑ ተናገሩ።