عن أنس رضي الله عنه، قال:
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم لأبي بكر وعمر: «هذان سَيِّدا كُهُول أهل الجنة من الأوَّلِين والآخِرين إلا النبيِّين والمرسلين».
[صحيح] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 3664]
المزيــد ...
ከአነስ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለአቡበከርና ዑመር እንዲህ አሉ: "እነዚህ ሁለቱ ከነቢያትና መልክተኞች ውጪ ከመጀመሪያው እስከመጨረሻው ካሉ የጀነት ነዋሪ ጎልማሶች አለቆቹ ናቸው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 3664]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አቡበከር አስሲዲቅንና ዑመር አልፋሩቅን (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢያት በኋላ ከሰው ዘር ሁሉ በላጮች እንደሆኑና ከነቢያትና መልክተኞች በኋላም ጀነት ከገቡ ሰዎች በላጮቹ መሆናቸውን ተናገሩ።