عن جابر رضي الله عنهما قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
«لن يدخلَ النارَ رجلٌ شَهِد بدرًا والحُدَيْبِيَة».
[صحيح] - [رواه أحمد، وأصله في صحيح مسلم] - [مسند أحمد: 15262]
المزيــد ...
ከጃቢር ቢን ዐብደላህ ረዲየሏሁ ዐንሁማ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል:
"በድርና ሑደይቢያ ላይ የተሳተፈ ሰው እሳት አይገባም።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሙስነድ አሕመድ - 15262]
ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሂጅራ በሁለተኛው ዓመት የተካሄደችውን የበድር ዘመቻ ከነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ጋር ሆኖ ለመዋጋት የተሳተፈና በስድስተኛው አመተ ሂጅራ የተከሰተችውን የውዴታው ቃልኪዳን የነበረበትን የሑደይቢያን ስምምነት የተሳተፈ ሰው እሳት እንደማይገባ ተናገሩ።