+ -

عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الخُدْرِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لاَ تَسُبُّوا أَصْحَابِي، فَلَوْ أَنَّ أَحَدَكُمْ أَنْفَقَ مِثْلَ أُحُدٍ ذَهَبًا مَا بَلَغَ مُدَّ أَحَدِهِمْ، وَلاَ نَصِيفَهُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 3673]
المزيــد ...

ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፦ «የአላህ መልክተኛ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል፦
"ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከናንተ መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ አምሳያ የሚያህል ቢመፀውት የአንዳቸውንም እፍኝ ሆነ የእፍኙን ግማሽ የመፀወቱት ጋር አይደርስም።"»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 3673]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሶሐቦችን ከመሳደብ ከለከሉ። በተለይ የመጀመሪያ ቀዳሚ የሆኑትን ሙሃጂሮችና አንሷሮችን መሳደብን ከለከሉ። ከሰዎች መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ የሚያህል ወርቅ ቢመፀውት የሚያገኘው ምንዳ አንድ ሶሐባ አንድ እፍኝ እህል ‐እፍኝ የተባለው መካከለኛ ሰው በሁለት እጆቹ የሚዘግነው መጠን ነው።‐ ወይም የእፍኙን ግማሽ እህል ቢመፀውት የሚያገኘው ምንዳ ጋር እኩል እንደማይሆን ተናገሩ። ይህም ከፍተኛ ኢኽላስ ስላላቸው፣ መካ ከመከፈቱ በፊት መመፅወት እጅግ አስፈላጊ በሆነበት በዛ ወቅት በመመፅወታቸውና በመዋጋታቸው ስለቀደሙ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ፈረንሳይኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Malagasisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሶሐቦችን (ረዲየሏሁ ዐንሁም) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና ‐ መሳደብ ክልክልና ከትላልቅ ወንጀሎች መካከል እንደሚመደብ እንረዳለን።