عن عمران بن حصين رضي الله عنه قال: كَانَتْ بِي بَوَاسِيرُ، فَسَأَلْتُ النَّبِيَّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنِ الصَّلَاةِ، فَقَالَ:
«صَلِّ قَائِمًا، فَإِنْ لَمْ تَسْتَطِعْ فَقَاعِدًا، فَإِنْ لَمْ تَسْتَطِعْ فَعَلَى جَنْبٍ».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 1117]
المزيــد ...

ከዒምራን ቢን ሑሰይን -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አለ: "ኪንታሮት ነበረብኝና ስለ አሰጋገዴ ነቢዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠየቅኳቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉኝ:-
'ቁመህ ስገድ! ካልቻልክ ተቀምጠህ ስገድ! ካልቻልክ በጎንህ ተጋድመህ ስገድ። '"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1117]

ማብራሪያ

መቆም ባልተቻለበት ወቅት ካልሆነ በቀር ለሶላት አሰጋገድ መሰረቱ መቆም እንደሆነና መቆም ካልቻለ ተቀምጦ እንደሚሰግድ ተቀምጦ መስገድም ካልቻለ በጎኑ ተጋድሞ መስገድ እንደሚችል ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ገለፁ።

ከሐዲሡ የሚቀሰሙ ቁምነገሮች

  1. በአቅም ልክ ከሁኔታ ወደ ሁኔታ መሸጋገር እንጂ አይምሮ ጤነኛ እስከሆነ ድረስ ሶላት የማትቀር ግዴታ ናት።
  2. አንድ ሰው አምልኮን የሚፈፅመው በአቅሙ ልክ መሆኑ የኢስላምን ገርነትና ቀላልነትን ያስረዳናል።
ትርጉሞችን አሳይ
ቋንቋ: الإنجليزية الأوردية الإسبانية ተጨማሪ (63)