عن أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ النَّبِيُّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«تَسَحَّرُوا، فَإِنَّ فِي السَّحُورِ بَرَكَةً».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1923]
المزيــد ...
ከአነስ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1923]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሰሑር ጉዳይ አነሳሱ። እርሱም ለጾም ዝግጅት ሌሊቱ መጨረሻ ላይ መመገብ ነው። በሌሊቱ መጨረሻ ወቅት ለሰሑርና ለዱዓእ መቆም (በረከት) - ማለትም ብዙ ምንዳና አጅር - ያስገኛል። ለጾም ያነቃቃል፤ ክብደቱንም ያቀላል።