عَنْ زَيْدِ بْنِ ثَابِتٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ قَالَ:
تَسَحَّرْنَا مَعَ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، ثُمَّ قَامَ إِلَى الصَّلاةِ، قُلْتُ: كَمْ كَانَ بَيْنَ الأَذَانِ وَالسَّحُورِ؟ قَالَ: قَدْرُ خَمْسِينَ آيَةً.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1921]
المزيــد ...
ከዘይድ ቢን ሣቢት - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
«ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጋር ሰሑር በላን። ከዚያም ወደ ሶላት ቆሙ። እኔም (አነስም ለዘይድ) "በአዛንና በሰሑር መካከል ምን ያክል ወቅት ነበር?" አልኩኝ። እርሱም (ዘይድም)፦ "ሃምሳ አንቀፅ የሚቀራበት ያህል" አለኝ።»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1921]
አንዳንድ ሶሐባዎች - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጋር ሰሑር በሉ። ከዚያም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ለፈጅር ሶላት ቆሙ። አነስም ለዘይድ ቢን ሣቢት - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "በአዛንና ሰሑር ተመግባቹ ባጠናቀቃችሁበት ወቅት መካከል ምን ያህል ጊዜ ነበር?" ብሎ ጠየቀው። ዘይድም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - "ረጅምም አጭርም፣ በፍጥነት አነባበብም ዝግ ያለ አነባበብም ሳይሆን በመካከለኛ አቀራር ሀምሳ አንቀጾችን የሚያስቀራ ያህል ጊዜ ነበር።" ብሎ መለሰ።