عَنْ أَبِي سَعِيدٍ الْخُدْرِيِّ رضي الله عنه قَالَ:
كُنَّا نُخْرِجُ إِذْ كَانَ فِينَا رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ زَكَاةَ الْفِطْرِ، عَنْ كُلِّ صَغِيرٍ وَكَبِيرٍ، حُرٍّ أَوْ مَمْلُوكٍ، صَاعًا مِنْ طَعَامٍ، أَوْ صَاعًا مِنْ أَقِطٍ، أَوْ صَاعًا مِنْ شَعِيرٍ، أَوْ صَاعًا مِنْ تَمْرٍ، أَوْ صَاعًا مِنْ زَبِيبٍ، فَلَمْ نَزَلْ نُخْرِجُهُ حَتَّى قَدِمَ عَلَيْنَا مُعَاوِيَةُ بْنُ أَبِي سُفْيَانَ رضي الله عنه حَاجًّا، أَوْ مُعْتَمِرًا فَكَلَّمَ النَّاسَ عَلَى الْمِنْبَرِ، فَكَانَ فِيمَا كَلَّمَ بِهِ النَّاسَ أَنْ قَالَ: إِنِّي أَرَى أَنَّ مُدَّيْنِ مِنْ سَمْرَاءِ الشَّامِ، تَعْدِلُ صَاعًا مِنْ تَمْرٍ، فَأَخَذَ النَّاسُ بِذَلِكَ، قَالَ أَبُو سَعِيدٍ: فَأَمَّا أَنَا فَلَا أَزَالُ أُخْرِجُهُ كَمَا كُنْتُ أُخْرِجُهُ، أَبَدًا مَا عِشْتُ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 985]
المزيــد ...
ከአቡ ሰዒድ አልኹድሪይ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ ብለዋል:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመካከላችን ሳሉ ዘካተል ፊጥርን ለሁሉም ህፃንና አዋቂ፣ ነፃም ሆነ ወይም ባሪያ አንድ ቁና ከስንዴ ወይም አንድ ቁና የደረቀ ወተት (እርጎ) ወይም አንድ ቁና ከገብስ ወይም አንድ ቁና ከተምር ወይም አንድ ቁና ከዘቢብ እናወጣ ነበር። ሙዓዊያ ቢን አቢ ሱፍያን - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ለሐጅ ወይም ለዑምራ እኛ ዘንድ እስኪመጣ ድረስም በዚህ መልኩ ከማውጣት አልተወገድንም ነበር። ሙዓዊያም ለሰዎች ሚንበር ላይ ወጥቶ ተናገረ። ለሰዎች ከተናገረውም ነገሮች መካከል "እኔ የሻም ሁለት እፍኝ ስንዴ ከአንድ ቁና ተምር ጋር ይስተካከላል ብዬ አምናለሁ።" የሚል ነበር። ሰዎችም የርሱን ንግግር ተመርኩዘው እርሱ ባለው ተገበሩ። አቡ ሰዒድም "እኔ ግን በህይወት እስከኖርኩ ድረስ በፊት አወጣው እንደነበረው ከማውጣት አልወገድም።" አለ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 985]
ሙስሊሞች በነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘመንና ከርሳቸው በኋላም በቅን ኸሊፋዎቹ ዘመን ዘካተል ፊጥርን ለትንሹም ሆነ ለትልቁ አንድ ቁና ስንዴ ያወጡ ነበር። በዛን ወቅት ምግባቸው ገብስ፣ (ዘቢብ) የደረቀ ወይን፣ ("አቂጥ") የደረቀ ወተት (እርጎ)ና ተምር ነበር። የአንድ ቁና መጠን በእፍኝ ሲሰላ አራት እፍኝ ነው። እፍኝ ማለት ደግሞ መካከለኛ እጅ ያለው ወንድ በሁለት እጁ ሙሉ ማለት ነው። ሙዓዊያ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ኸሊፋ በነበሩበት ወቅት ወደ መዲና ሲመጡ በጊዜውም የሻም ስንዴ የበረከተበት ወቅት ነበረና ኹጥባ አደረጉ፡ "የሻም ስንዴ ሁለት እፍኝ (ግማሽ ቁና) ከአንድ ቁና ተምር ጋር ይስተካከላል ብዬ አምናለሁ።" አሉ። ሰዎችም በርሳቸው አቋም ላይ ተገበሩ። አቡ ሰዒድ አልኹድሪይም - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንዲህ አሉ፡ "እኔ ግን እስከኖርኩ ድረስ በነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዘመን አወጣው የነበርኩትን ያህል ማውጣቴን አላቆምም።"