+ -

عَنِ ابْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ:
فَرَضَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ زَكَاةَ الفِطْرِ صَاعًا مِنْ تَمْرٍ، أَوْ صَاعًا مِنْ شَعِيرٍ، عَلَى العَبْدِ وَالحُرِّ، وَالذَّكَرِ وَالأُنْثَى، وَالصَّغِيرِ وَالكَبِيرِ مِنَ المُسْلِمِينَ، وَأَمَرَ بِهَا أَنْ تُؤَدَّى قَبْلَ خُرُوجِ النَّاسِ إِلَى الصَّلاَةِ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1503]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
"የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ይስፈንና ዘካተል ፊጥርን አንድ ቁና ከተምር ወይም አንድ ቁና ከገብስ ማውጣትን በባሪያውም፣ በነፃውም፣ በወንዱም፣ በሴቱም፣ በህፃኑም፣ በትልቁም ሙስሊም ላይ ግዴታ አደረጉ። ሰዎች ወደ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1503]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከረመዷን በኋላ ዘካተል ፊጥርን ግዴታ አደረጉ። መጠኑም አራት እፍኝ የሚያህል አንድ ቁና ነው። አንድ እፍኝ፡ ማለት የመካከለኛ ሰው መዳፍ የሚሞላ ነው። ግዴታ ያደረጉትም ሁሉም ነፃ፣ ባሪያ፣ ወንድ፣ ሴት፣ ህፃን፣ ትልቅ ሙስሊም ላይ ከተምር ወይም ከገብስ እንዲሰጡ ነው። ይህም እርሱ ዘንድ ያለው ከቀንና ከምሽት ቀለቡ የሚተርፍ በሆነ ላይ ለነፍሱና ለሚያስተዳድራቸው ሁሉ ነው። ሰዎች ወደ ዒድ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የረመዷንን ዘካተል ፊጥር ለህፃን፣ ለትልቅ፣ ለነፃ፣ ለባሪያ ማውጣቱ ግዴታ ነው። እንዲያወጣ የሚጠየቀውም የቤት ሃላፊውና አስተዳዳሪው ነው። ሰውዬው ለራሱ፣ ለልጆቹና ቀለባቸው ግዴታ ለሆነበት አካላት የማውጣት ግዴታ አለበት።
  2. ዘካተል ፊጥርን ለፅንስ ማውጣት ግዴታ አይደለም። ይልቁንም ተወዳጅ ነው።
  3. ለዘካተል ፊጥር የሚወጣው ነገር ምንነቱ መገለፁ፤ እርሱም የተለመደውን የሰዉ ቀለብ ነው።
  4. ዘካተል ፊጥርን ከዒድ ሶላት በፊት ማውጣት ግዴታ ነው። በላጩ የዒድ ንጋት ላይ ማውጣት ነው። ይሁን እንጂ ከዒዱ ቀን አንድ ቀን ወይም ሁለት ቀን ቀደም ብሎ ማውጣትም ይፈቀዳል።