+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«لَا تَقَدَّمُوا رَمَضَانَ بِصَوْمِ يَوْمٍ وَلَا يَوْمَيْنِ إِلَّا رَجُلٌ كَانَ يَصُومُ صَوْمًا فَلْيَصُمْهُ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1082]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) እንዲህ ብለዋል:
"ከረመዷን አንድ ቀንም ሆነ ሁለት ቀን በፊት ቀድማቹህ አትፁሙ። ነገር ግን ያስለመደው ጾም የነበረበት ሰው ከሆነ ይፁመው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1082]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም ለረመዷን ጥንቃቄ ብሎ ረመዷን ከመግባቱ ከአንድ ቀን ወይም ከሁለት ቀን በፊት መጾምን ከለከሉ። ምክንያቱም የረመዷን ጾም ግዴታነት የተያያዘው ጨረቃን ከመመልከት ጋር ነውና። ስለዚህ መጨናነቅ አያስፈልግም። ነገር ግን አንድ ቀን እየጾመ አንድ ቀን የመብላት ልምድ ያለው ወይም ሰኞና ሀሙስ የመጾም ልምድ ያለው አይነቱ ሰው ከሆነ ከዚህ ልምዱ ጋር ከገጠመ መጾም ይችላል። ይህም በምንም መልኩ የረመዷን አቀባበል ስላልሆነ ነው። እንደስለትና የቀዷእ (ያመለጠን ግዴታ ፆም ማካካሻ) ጾም የመሰሉ ግዴታ ጾሞች እዚህ (የተፈቀደው) ውስጥ ይካተታሉ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. እራስን ማስጨነቅ መከልከሉንና ያለምንም ጭማሪና ማጓደል በተደነገገው መልኩ አምልኮ በመፈፀም ላይ መጠባበቅ ግዴታ መሆኑን እንረዳለን።
  2. የዚህ ጥበብ ምክንያትም -አላህ ይበልጡን ያውቃል- ግዴታ አምልኮዎችን ከሱንና (ግዴታ ካልሆኑ) አምልኮዎች ለመለየት፤ ለረመዷን በንቃትና በተነሳሽነት እንዲዘጋጅ እና ጾም የዚህ ታላቅ ወር መገለጫ እንዲሆን ሲባል ነው።
ተጨማሪ