عَنْ أَبِي عُبَيْدٍ، مَوْلَى ابْنِ أَزْهَرَ، قَالَ:
شَهِدْتُ العِيدَ مَعَ عُمَرَ بْنِ الخَطَّابِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ، فَقَالَ: هَذَانِ يَوْمَانِ نَهَى رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنْ صِيَامِهِمَا: يَوْمُ فِطْرِكُمْ مِنْ صِيَامِكُمْ، وَاليَوْمُ الآخَرُ تَأْكُلُونَ فِيهِ مِنْ نُسُكِكُمْ.
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 1990]
المزيــد ...
ኢብኑ አዝሃር ነፃ ያወጡት ባሪያ ከሆነው ከአቡ ዑበይድ እንደተላለፈው እንዲህ አለ:
«ዒድን ከዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጋር ለመስገድ ተገኘሁ። እንዲህም አሉ: "እነዚህ ሁለት ቀናቶች የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመጾም የከለከሉት ቀናቶች ናቸው። (እነርሱም) ከጾማችሁ የምትፈቱበት ቀን (ዒድ አልፊጥር) እና ሌላኛው ቀን ደግሞ ከእርዳችሁ የምትበሉበት የሆነው ቀን (ዒደል አድሓ) ናቸው።"»
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 1990]
ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ዒደል ፊጥርና ዒደል አድሓን ከመጾም ከለከሉ። ዒደል ፊጥር ከረመዳን ወር ጾም የሚፈታበት ቀን ስለሆነ ነው። የዒደል አድሓ ቀን ደግሞ ከኡድሒያው ስጋ የሚበላበት ቀን ስለሆነ ነው።