+ -

عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ عُمَرَ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا:
أَنَّ تَلْبِيَةَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «لَبَّيْكَ اللهُمَّ، لَبَّيْكَ، لَبَّيْكَ لَا شَرِيكَ لَكَ لَبَّيْكَ، إِنَّ الْحَمْدَ وَالنِّعْمَةَ لَكَ وَالْمُلْكَ لَا شَرِيكَ لَكَ» قَالَ: وَكَانَ عَبْدُ اللهِ بْنُ عُمَرَ رَضِيَ اللهُ عَنْهُمَا يَزِيدُ فِيهَا: لَبَّيْكَ لَبَّيْكَ، وَسَعْدَيْكَ، وَالْخَيْرُ بِيَدَيْكَ، لَبَّيْكَ وَالرَّغْبَاءُ إِلَيْكَ وَالْعَمَلُ.

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1184]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ተልቢያቸው "ለበይከ አልላሁምመ ለበይክ፣ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣ ኢነልሐምደ ወንኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላ ሸሪከ ለክ" (አላህ ሆይ! ደግሜ ደጋግሜ ለጥሪህ አቤት እላለሁ፤ ምንም ተጋሪ የለህም። ምስጋና ፀጋና ንግስና ለአንተ ብቻ ነው፤ ምንም ተጋሪ የለህም።) የሚል ነበር። ዐብደላህ ቢን ዑመር -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እዚህ ላይ "ለበይከ ለበይከ ወሰዕደይክ፣ ወልኸይሩ ቢየደይክ፣ ለበይከ ወርረግባኡ ኢለይከ ወልዐመል" (ጥሪህን ተቀብያለሁ፣ ለጥሪህ ምላሽ እሰጣለሁ፣ መልካም ነገር ሁሉ በእጅህ ነው፤ ምኞትና ተግባር ወደ አንተ ይመራል።) የሚለውን ይጨምሩ ነበር።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1184]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ወደ ሐጅ ወይም ዑምራ ተግባር መግባት ሲፈልጉ ይሉት የነበረው ተልቢያ እንዲህ ብለው ነበር: (ለበይከ አልላሁመ ለበይክ) አላህ ሆይ! ወደ ጠራኸን ተውሒድ፣ ስራን ለአላህ ማጥራት፣ ለሐጅና ለሌሎችም አምልኮዎች ቁርጠኛ የሆነ መቀበልን ደጋግሜ ተቀብያለሁ። (ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ) አንተ ብቻ ነህ አምልኮ የሚገባህ፣ በጌትነትህ፣ በተመላኪነትህና በስሞችህና በባህሪያቶችህም አጋር የለህም። (ኢነል ሐምደ) ምስጋናና ውዳሴ ላንተ ነው የሚገባህ። (ወንኒዕመተ) ፀጋም (ለከ) ከአንተ ነው። አንተው ነህ የምትሰጠን። በሁሉም ሁኔታዎች የምታስተናብረው አንተ ነህ። (ወልሙልኩ) ንግስናም ያንተ ነው። (ላሸሪከ ለክ) የሚጋራህ የሌለ ሁሉም ያንተ ብቻ ነው። ኢብኑ ዑመር - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እዚህ ተልቢያ ላይ ይህን ይጨምሩ ነበር፡ (ለበይከ ለበይከ ወሰዕደይክ) ደጋግሜ ጥሪህን እቀበላለሁ፤ አስደስተኝ። (ወልኸይሩ ቢየደይክ) ሁሉም መልካም የሚገኘው በችሮታህ ነው። (ለበይከ ወርረግባኡ ኢለይክ) ልመናና ፍላጎታችንም የምንፈልገው መልካም ነገርም በእጅህ ወደሆንከው ወዳንተ ነው። (ወልዐመሉ) ስራም ለአንተ ነው። አምልኮ የሚገባው ለአንተ ብቻ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሐጅና ዑምራ ላይ ተልቢያ የተደነገገ መሆኑንና አፅንዖት የተሰጠው መሆኑን እንረዳለን። ተክቢራ የሶላት መገለጫ እንደሆነው ሁሉ ተልቢያም በሐጅና ዑምራ ወቅት ልዩ መገለጫው ነው።
  2. ኢብኑል ሙኒር እንዲህ ብለዋል: "ተልቢያ መደንገጉ አላህ ባሮቹን ምን ያህል እንዳከበረ ያስገነዝበናል። ይህም ወደ ቤቱ ጉብኝት ማድረጋቸው በአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ጥሪ እንደሆነ ስለሚጠቁም ነው።"
  3. በላጩ ተልቢያ ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ያደረጉትን ተልቢያ ማለት ነው። ቢጨምርም ግን ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ያፀደቁት ስለሆነ ችግር የለውም። ኢብኑ ሐጀር እንዲህ ብለዋል: "ይህ ሚዛናዊው መንገድ ነው። ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የመጣውን ለብቻው ይልና ከሶሐባ የመጣን ወይም ቦታው ላይ የሚመጥን በራሱ ማለት የሚፈልገውን ለማለት የፈለገ ጊዜ ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመጣው ጋር በማይቀላቀል መልኩ ለብቻው ይለዋል። ይህ ተልቢያ ተሸሁድ ላይ ከመጣው ዱዓ ጋር ይመሳሰላል። ነቢዩ በተሸሁድ ዱዓ ዙሪያ እንዲህ ብለዋል፡ "ከዚያም የሻውን ዱዓና ውዳሴ ይምረጥ።" ማለትም ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የመጣውን ከጨረሰ በኋላ ነው።"
  4. በተልቢያ ድምፅን ከፍ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን። ይህም ለወንድ ነው። ሴት ከሆነች ግን ፈተናን ስለሚያሰጋ ድምጿን ዝግ ታደርጋለች።
ተጨማሪ