عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«كُلُّ أُمَّتِي مُعَافًى إِلَّا المُجَاهِرِينَ، وَإِنَّ مِنَ المُجَاهَرَةِ أَنْ يَعْمَلَ الرَّجُلُ بِاللَّيْلِ عَمَلًا، ثُمَّ يُصْبِحَ وَقَدْ سَتَرَهُ اللَّهُ عَلَيْهِ، فَيَقُولَ: يَا فُلاَنُ، عَمِلْتُ البَارِحَةَ كَذَا وَكَذَا، وَقَدْ بَاتَ يَسْتُرُهُ رَبُّهُ، وَيُصْبِحُ يَكْشِفُ سِتْرَ اللَّهِ عَنْهُ».

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: እንዲህ አለ: "የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ፦
'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል። ይፋ ከማውጣትም መካከል ሰውዬው ምሽት ላይ አንድ ወንጀልን ይሰራል ከዚያም አላህ በርሱ ላይ (ወንጀሉን) ሸሽጎለት አንግቶ ሳለ ‹እከሌ ሆይ! ትናንት ምሽት እንዲህ እንዲህ ሰራሁ።› ይላል። ጌታው (ወንጀሉን) ሸሽጎለት አድሮ ሳለ የአላህን ግርዶሽ ከራሱ ላይ የሚገፍ ሆኖ ያነጋል።"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሙስሊም ወንጀለኛ ወንጀሉን በፉከራና በብልግና ይፋ የሚያወጣ ካልሆነ በቀር የአላህን ይቅርታና ምህረት የማግኘት ተስፋ እንዳለው ገለፁ። ወንጀሉን ይፋ የሚያደርግ ግን ይቅርታ አይገባውም። ምሽት ላይ ወንጀል ይሰራል ከዚያም አላህ ሸሽጎለት አንግቶ ሳለ ለሌላ ሰው ትናንት የሆነች ወንጀልን እንደሰራ ይናገራል። ጌታው ሸሽጎለት አድሮ ሳለ የአላህን ግርዶሽ የገለጠ ሆኖ ያነጋል።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ሩስያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ታጋሎግ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. አላህ በርሱ ላይ ከሸሸገለት በኋላ ወንጀልን ይፋ ማውጣት ፀያፍ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ወንጀልን ይፋ ማድረግ በአማኞች መካከል ብክለት እንዲሰራጭ ያደርጋል።
  3. አላህ በዱንያ የሸሸገው ሰው በመጨረሻው አለምም ይሸሽገዋል። ይህም አላህ በባሮቹ ላይ ካለው እዝነት ስፋት ነው።
  4. በወንጀል የተፈተነ ሰው ወንጀሉን በራሱ ሸሽጎ ወደ አላህ መመለስ ይገባዋል።
  5. ወንጀላቸውን ይፋ የሚያደርጉ ሰዎች ወንጀል ትልቅ መሆኑን እንረዳለን። እነሱም ወንጀላቸውን ይፋ ማድረግን በማሰብ ለነፍሳቸው ይቅርታን ያስመለጡ ናቸው።