+ -

عَنْ سَعْدِ بنِ أبي وَقَّاصٍ رَضيَ اللهُ عنه قَالَ:
كُنَّا عِنْدَ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ، فَقَالَ: «أَيَعْجِزُ أَحَدُكُمْ أَنْ يَكْسِبَ، كُلَّ يَوْمٍ أَلْفَ حَسَنَةٍ؟» فَسَأَلَهُ سَائِلٌ مِنْ جُلَسَائِهِ: كَيْفَ يَكْسِبُ أَحَدُنَا أَلْفَ حَسَنَةٍ؟ قَالَ: «يُسَبِّحُ مِائَةَ تَسْبِيحَةٍ، فَيُكْتَبُ لَهُ أَلْفُ حَسَنَةٍ، أَوْ يُحَطُّ عَنْهُ أَلْفُ خَطِيئَةٍ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2698]
المزيــد ...

ከሰዕድ ቢን አቢ ወቃስ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላችውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዘንድ ነበርን። እንዲህም አሉን: "አንዳችሁ በየቀኑ አንድ ሺህ ምንዳ መሸመት ይሳነዋልን?" ከተቀመጡት ሰዎች መካከል አንድ ጠያቂ "እንዴት ነው አንዳችን አንድ ሺህ ምንዳ የሚሸመተው?" በማለት ጠየቃቸው። እርሳቸውም: "መቶ ጊዜ ተስቢሕ ካለ ለርሱ አንድ ሺህ ምንዳ ይፃፍለታል ወይም ከርሱ ላይ አንድ ሺህ ወንጀል ይሰረዝለታል።" በማለት መለሱ።»

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2698]

ትንታኔ

ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ባልደረቦቻቸውን እንዲህ በማለት ጠየቁ: አንዳችሁ በየቀኑ አንድ ሺህ ምንዳ ማግኘት አይችልምን? እዛው ከተቀመጡት መካከል አንዱ "አንድ ሰው በቀላሉ በየቀኑ አንድ ሺህ ምንዳ እንዴት ሊያገኝ ይችላል?" በማለት ጠየቀ። እርሳቸውም "መቶ ጊዜ ሱብሓነላህ ይበል። በዚህም አንድ ሺህ ምንዳ ይፃፍለታል።" አሉ። አንድ መልካም ስራ በአስር ትባዛለችና። ወይም አንድ ሺህ ወንጀሉ ይራገፍለታል።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ትርፍ ስራዎችን በመስራት ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን። ይህም ትርፍ ስራዎች ወደ አምልኮዎች የሚወስዱ መሰላል ስለሆኑ ነው።
  2. ተስቢሕና ዚክር የማድረግን ደረጃ እንረዳለን። ይህም ሰው በማይከብደው ትንሽ ስራ አማካኝነት ይህንን ያህል ትልቅ ምንዳ ያስገኛልና።
  3. ሶሓቦች መልካም ስራዎችን ሳያዘገዩ ለመስራት ይቻኮሉ እንደነበረ እንረዳለን።
  4. መልካም ስራዎች በአስር ይባዛሉ። ይህንንም በማስመልከት አላህ እንዲህ ብሏል: (በመልካም ስራ የመጣ ሰው ለርሱ አስር ብጤዎቿ አሉት።) [አልአንዓም: 160] ይህም ትንሹ የብዜት ደረጃ ነው። እንጂማ እስከ ሰባት መቶ እጥፍ ድረስ እንደሚባዛም ተዘግቧል።
  5. በዚህ ሐዲሥ አንዳንድ ዘገባዎች (ወይም ከርሱ አንድ ሺህ ወንጀል ይሰረዝለታል።) ከሚለው ነቢያዊ ንግግር (ወይም) የሚለው ቃል ሳይጠቀስ (و) (ሁለቱንም እንደሚያገኝ በሚጠቁም መስተፃምር) መጥቷል። ቃሪይ እንዲህ ብለዋል: "አንዳንዴ (و) (ወይም) የሚለውን ትርጉም ለመጠቆም ትመጣለች። በሁለቱ ዘገባዎች መካከል መጋጨት የለውም። ትርጉሙም: ይህቺን ዚክር ያለ ሰው በርሱ ላይ ወንጀል ከሌለበት አንድ ሺህ ምንዳ ይፃፍለታል። በተወሰነው ይሰረዝለታል በተወሰነው ይፃፍለታል ማለት ነው። ወይም ደግሞ (ወይም) በአረብኛው (او) የምትለዋ ቃል የተፈለገባት (و) ወይም (بل) ማለት ነው። ይህ ከሆነ ደግሞ ይህንን ዚክር ያለ ሰው ሁለቱንም ያገኛል ማለት ነው። የአላህ ችሮታ ከዚህም በላይ ነውና።" ተጠናቀቀ። ማለትም አንድ ሺህ ምንዳም ያገኛል። አንድ ሺህ ወንጀሉም ይሰረዝለታል እንደማለት ነው።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ