+ -

عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضيَ اللهُ عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ قَالَ:
«اللهُمَّ لَا عَيْشَ إِلَّا عَيْشُ الْآخِرَهْ، فَاغْفِرْ لِلْأَنْصَارِ وَالْمُهَاجِرَهْ».

[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح مسلم: 1805]
المزيــد ...

ከአነስ ቢን ማሊክ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- እንዲህ ብለዋል፦
"አላህ ሆይ! ከመጪው አለም ኑሮ ውጪ ኑሮ የለም። ለአንሷሮችና ሙሃጂሮች ማራቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1805]

ትንታኔ

ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እውነተኛ ኑሮ በመጪው አለም በአላህ ውዴታ፣ እዝነትና ጀነት ውስጥ ያለው ነው እንጂ ሌላ ትክክለኛ ኑሮ እንደሌለ ተናገሩ። የዱንያ ኑሮ ተወጋጅ ነው። የመጪው አለም ኑሮ ዘውታሪና ቀሪ ነው። ቀጥለውም ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ምህረትን፣ መከበርንና መልካምነትን ለእነዚያ ነቢዩን - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - እና ሙሃጂሮችን ላስጠጉትና ገንዘባቸውን ላካፈሉት አንሷሮች በተጨማሪ የአላህን ውዴታና ችሮታ ፈልገው ሃገራቸውንና ገንዘባቸውን ትተው ለተሰደዱት ዱዓ አደረጉላቸው።

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ለዱንያ የነበራቸው ቸልተኝነትንና ሙሉ ለሙሉ ወደ መጪው አለም ራሳቸውን ያዞሩ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ጠፊ ከሆነው የዱንያ ጥቅም ኡመታቸው ችላ እንዲል መጣራቸውን እንረዳለን።
  3. ሙሃጂሮችና አንሷሮች ምህረት እንዲያገኙ በነቢዩ - የአላህ ሶላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይስፈንና - ዱዓ የተደረገላቸው በመሆናቸው የነርሱ ማዕረግ ከፍታ ተገልፆ እንመለከታለን።
  4. አንድ ሰው በሚያገኘው የዱንያ መጣቀሚያ መደሰት የለበትም። ዱንያ ውስጧ ካሉት መከራዎችም ጋር ለመጥፋት ቅርብ ናትና። የመርጋትና የመዘውተርያ አገር የመጪው አለም አገር ነው።
ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ አሳምኛ الدرية الرومانية المجرية الجورجية الخميرية الماراثية
ትርጉሞችን ይመልከቱ