عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«لَا يَسْتُرُ عَبْدٌ عَبْدًا فِي الدُّنْيَا إِلَّا سَتَرَهُ اللهُ يَوْمَ الْقِيَامَةِ».
[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2590]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ብለዋል፦
" አንድ ባሪያ የአንድን ባሪያ ነውር በዱንያ አይሸፍንም፤ የትንሳኤ ቀን አላህ ነውሩን የሚሸፍንለት ቢሆን እንጂ።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2590]
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አንድ ሙስሊም የሙስሊም ወንድሙን ነውር የሚሸፍን ከሆነ አላህ የትንሳኤ ቀን የርሱን ጉዳይ የሚሸፍንለት መሆኑን ገለፁ። የስራ ክፍያ እንደስራው አይነት ነው። አላህ ነውሩን የሚሸፍንለት ነውሩንና ወንጀሉን ከተቀሰቀሱ ፍጡራን በመሸሸግ ነው። በዛ ወንጀል መተሳሰብና ለርሱ ማውሳቱን በመተውም ሊሆን ይችላል።