عَنْ ‌قَتَادَةَ رحمه الله قال:
حَدَّثَنَا ‌أَنَسُ بْنُ مَالِكٍ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ أَنَّ رَجُلًا قَالَ: يَا نَبِيَّ اللهِ كَيْفَ يُحْشَرُ الْكَافِرُ عَلَى وَجْهِهِ؟ قَالَ: «أَلَيْسَ الَّذِي أَمْشَاهُ عَلَى الرِّجْلَيْنِ فِي الدُّنْيَا قَادِرًا عَلَى أَنْ يُمْشِيَهُ عَلَى وَجْهِهِ يَوْمَ الْقِيَامَةِ؟» قَالَ قَتَادَةُ: بَلَى وَعِزَّةِ رَبِّنَا.

[صحيح] - [متفق عليه]
المزيــد ...

ቀታዳህ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
አነስ ቢን ማሊክ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደነገሩን አንድ ሰው "የአላህ ነቢይ ሆይ! ከሓዲዎች በትንሣኤ ቀን እንዴት በፊቶቻቸው እየተሳቡ ይቀሰቀሳል?"አላቸው። እርሳቸውም " ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?" አሉት። ቀታዳህ እንዲህ አሉ፦ "በጌታዬ ልቅና ይሁንብኝ እንዴታ!"

Sahih/Authentic. - [Al-Bukhari and Muslim]

ትንታኔ

ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ከሓዲዎች በትንሣኤ ቀን እንዴት በፊቶቻቸው እየተሳቡ ይቀሰቀሳል?" ተብለው ተጠየቁ። ነቢዩም የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን "ያ በዱንያ ውስጥ እያሉ በሁለት እግራቸው እንዲሄዱ ያደረጋቸው አላህ የትንሳኤ ቀን በፊታቸው እንዲሄዱ ማድረግ የሚችል አይደለምን?" በማለት መለሱ። አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነውና።

ትርጉም: እንግሊዝኛ ፈረንሳይኛ ስፔንኛ ቱርክኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ቦስንያኛ ባንጋሊኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ህንድኛ ቬትናማዊ ሲንሃላዊ ኡይጙራዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية الدرية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. የትንሳኤ ቀን የከሀዲያን ውርደት፤ ከሀዲ በፊቱ እየተሳበ ነው የሚሄደው።