+ -

‌عن عَلِيٍّ قَالَ: إِنِّي كُنْتُ رَجُلًا إِذَا سَمِعْتُ مِنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ حَدِيثًا نَفَعَنِي اللهُ مِنْهُ بِمَا شَاءَ أَنْ يَنْفَعَنِي بِهِ، وَإِذَا حَدَّثَنِي رَجُلٌ مِنْ أَصْحَابِهِ اسْتَحْلَفْتُهُ، فَإِذَا حَلَفَ لِي صَدَّقْتُهُ، وَإِنَّهُ حَدَّثَنِي ‌أَبُو بَكْرٍ، وَصَدَقَ أَبُو بَكْرٍ، قَالَ: سَمِعْتُ رَسُولَ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«مَا مِنْ رَجُلٍ يُذْنِبُ ذَنْبًا، ثُمَّ يَقُومُ فَيَتَطَهَّرُ، ثُمَّ يُصَلِّي، ثُمَّ يَسْتَغْفِرُ اللهَ، إِلَّا غَفَرَ اللهُ لَهُ»، ثُمَّ قَرَأَ هَذِهِ الْآيَةَ: {وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنْفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ} [آل عمران: 135].

[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي في الكبرى وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 406]
المزيــد ...

ከዐሊይ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: "እኔ ከአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አንድን ሐዲሥ የሰማሁ ጊዜ አላህ በዛ ሐዲሥ በሻው መንገድ የሚጠቅመኝ ሰው ነበርኩ፤ ከሶሐቦቻቸው መካከል አንድ ሰው ሐዲሥ የነገረኝ ጊዜ ታዲያ አስምለዋለሁ። ከማለልኝ አምነዋለሁ። አቡበከር ለኔ አንድ ሐዲሥ ነግሮኛል። አቡበከር የነገረኝም እውነት ነበር። አቡበከር እንዲህ አሉ: 'የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ:
"ኃጢዓትን የሠራ ከዚያም ተነስቶ ዉዱእ አድርጎ የሚሰግድ ከዚያም ለኃጢዓቱ ከአሏህ ምህረት የሚጠይቅ አንድም ሰው የለም፤ አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ።› ቀጥለውም ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለሀጢዐቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት} [ኣሊ ዒምራን:135] '"

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳወድ፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በኩብራ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 406]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አላህ ለርሱ የሚምረው ቢሆን እንጂ ዉዱእን አሳምሮ ከዚያም ከወንጀሉ ወደ አላህ በመመለስ ኒያ ቁሞ ሁለት ረከዓ ሰግዶ ከዚያም አላህን ምህረት የሚጠይቅ አንድም ኃጢዓት የሚሰራ ባሪያ እንደሌለ ተናገሩ። ቀጥለውም ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ይህንን የአላህ ቃል አነበቡ: {ለእነዚያም መጥፎ ስራን በሰሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለሀጢዐቶቻቸው ምህረትን የሚለምኑ ለሆኑት ከአላህም ሌላ ኀጢዐቶችን የሚምር አንድም የለ። (በስህተት) በሰሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲሆኑ የማይዘወትሩ ለሆኑት (ተደግሳለች)።} [ኣሊ ዒምራን:135]

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ሶላት ላይ እና ለወንጀል ምህረት መጠየቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. የአላህ ምህረት ሰፊ መሆኑንና፤ ተውበትና ምህረት ሲጠየቅ እንደሚቀበል እንረዳለን።