عَنْ عَائِشَةَ رَضِيَ اللهُ عَنْهَا قَالَتْ:
تَلَا رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ هَذِهِ الْآيَةَ: {هُوَ الَّذِي أَنْزَلَ عَلَيْكَ الْكِتَابَ مِنْهُ آيَاتٌ مُحْكَمَاتٌ هُنَّ أُمُّ الْكِتَابِ وَأُخَرُ مُتَشَابِهَاتٌ فَأَمَّا الَّذِينَ فِي قُلُوبِهِمْ زَيْغٌ فَيَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ ابْتِغَاءَ الْفِتْنَةِ وَابْتِغَاءَ تَأْوِيلِهِ، وَمَا يَعْلَمُ تَأْوِيلَهُ إِلَّا اللَّهُ، وَالرَّاسِخُونَ فِي الْعِلْمِ يَقُولُونَ آمَنَّا بِهِ كُلٌّ مِنْ عِنْدِ رَبِّنَا وَمَا يَذَّكَّرُ إِلَّا أُولُو الْأَلْبَابِ} [آل عمران: 7]. قَالَتْ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «فَإِذَا رَأَيْتِ الَّذِينَ يَتَّبِعُونَ مَا تَشَابَهَ مِنْهُ فَأُولَئِكَ الَّذِينَ سَمَّى اللهُ، فَاحْذَرُوهُمْ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 4547]
المزيــد ...
የምእመናን እናት ዓኢሻ -አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና- እንዲህ ብላለች፦
የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሀፉን ያወረደ ነው። ከእርሱ (ከመፅሀፉ) ግልጽ የሆኑ አንቀጾች አሉ። እነሱ የመጽሐፉ መሠረቶች ናቸው። ሌሎችም ተመሳሳዮች አሉ። እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን በመፈለግና ማጣመምን በለመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ። (ትክክለኛ) ፍቺውንም አላህ ብቻ እንጂ ሌላ አያውቀውም። በዕውቀትም የጠለቁት "በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው" ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም።} [ኣሉ ዒምራን: 7] ቀጥለው የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ አሉ፦ " እነዚያ ከቁርኣን የተመሳሰለውን የሚከተሉትን ከተመለከትሽ አላህ ተጠንቀቁዋቸው ብሎ የጠቀሳቸው እነሱ ናቸው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 4547]
የአላህ መልክተኛ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ይህቺን አንቀፅ አነበቡ {እርሱ ያ በአንተ ላይ መጽሀፉን ያወረደ ነው። ከእርሱ (ከመጽሐፉ) ግልጽ የሆኑ አንቀጾች አሉ። እነሱ የመጽሀፉ መሠረቶች ናቸው። ሌሎችም ተመሳሳዮች አሉ። እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው ሰዎች ማሳሳትን በመፈለግና ማጣመምን በመፈለግ ከርሱ የተመሳሰለውን ይከታተላሉ። (ትክክለኛ) ፍቺውንም አላህ ብቻ እንጂ ሌላ አያውቀውም። በዕውቀትም የጠለቁት "በርሱ አምነናል፤ ሁሉም ከጌታችን ዘንድ ነው" ይላሉ። የአእምሮ ባለቤቶችም እንጅ (ሌላው) አይገሰጽም።} አላህ በዚህ አንቀፅ ውስጥ በነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ላይ ቁርኣንን ያወረደው እርሱ አላህ መሆኑን ይናገራል። ከቁርኣን ውስጥም መልእክታቸው ግልፅ የሆኑና ያለምንም ማደናገር ድንጋጌያቸው የታወቁ አንቀፆች አሉ። እርሱም የመጽሐፉ መሰረትና በልዩነት ወቅት የሚዳኝ ምንጭ ነው። ቁርኣን ውስጥ በርካታ ትርጓሜን የሚሰጡ አሻሚ አንቀፆችም አሉ። እነዚህ አንቀፆችን አንዳንድ ሰዎች ወይ በትርጓው ይደናገራሉ ወይም ከሌላ አንቀፅ ጋር እንደተጋጨ ያስባሉ። ቀጥሎ አላህ ሰዎች ከነዚህ አንቀፆች ጋር ያላቸውን መስተጋብር አብራራ። እነዚያ ልቦቻቸውን ከሀቅ መጣመም የተጠናወተው ሰዎች ሰውን ማሳሳትና ብዥታን ማቀጣጠል በመፈለግ ግልፅ የሆኑትን አንቀፆች በመተው አሻሚ የሆኑትን አንቀፆች ይወስዳሉ። ይህንንም ያደረጉት ዝንባሌያቸውን በሚስማማ መልኩ መፍታትን በመፈለጋቸው ነው። በእውቀት የፀኑት ግን እነዚህን አሻሚ አንቀፆች ያውቃሉ ፍቻቸውንም ወደ ግልፅ አንቀፆች ይመልሳሉ፤ ከአላህ ዘንድ ስለሆነም እርስ በርስ ምንም መጋጨትና ማደናገር ሊከሰት እንደማይችል ያምናሉ። ነገር ግን የንፁህ አይምሮ ባለቤት ካልሆነ በቀር ሊገሰፅም ሆነ ሊመከር እንደማይችል አላህ ገለፀ። ቀጥለው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን ለአማኞች እናት ዓኢሻህ - አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና - "እነዚያ አሻሚ አንቀፆችን የሚከታተሉትን ከተመለከተች አላህ {እነዚያማ በልቦቻቸው ውስጥ ጥመት ያለባቸው} በማለት የጠቀሳቸው ናቸውና ተጠንቀቋቸው አታድምጧቸው።" አሏት።