+ -

عَنْ ‌عَدِيِّ بْنِ حَاتِمٍ عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ:
«الْيَهُودُ مَغْضُوبٌ عَلَيْهِمْ، وَالنَّصَارَى ضُلَّالٌ».

[صحيح] - [رواه الترمذي] - [سنن الترمذي: 2954]
المزيــد ...

ከዓዲይ ቢን ሓቲም እንደተላለፈው: "ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እንዲህ አሉ፦
"አይሁዶች ቁጣ የሰፈነባቸው ሲሆኑ ክርስቲያኖች ደግሞ የተሳሳቱ ናቸው።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2954]

ትንታኔ

ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አይሁዶች እውነትን እያወቁ ባለመተግበራቸው አላህ የተቆጣባቸው ህዝቦች እንደሆኑ ተናገሩ። ክርስቲያኖች ደግሞ ያለ ዕውቀት የሚሰሩ ስለሆኑ የተሳሳቱ ህዝቦች ናቸው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ቱርክኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht Oromisht Kannadisht الولوف Azerisht الأوكرانية الجورجية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ዕውቀትና ተግባርን ሰብስቦ መሄድ ቁጣ ከሰፈነባቸውም ከተሳሳቱትም ሰዎች መንገድ መዳኛ መሆኑን እንረዳለን።
  2. ከአይሁዶችና ክርስቲያኖች መንገድ መጠንቀቅና ቀጥተኛ የሆነውን የኢስላምን ጎዳና አጥብቀን መያዝ እንዳለብን እንረዳለን።
  3. በመሰረቱ አይሁዶችም ክርስቲያኖችም የተሳሳቱና ቁጣ የሰፈነባቸው ህዝቦች ናቸው። ነገር ግን ልዩ መገለጫቸው የአይሁዶቹ ቁጣ የሰፈነባቸው መሆናቸው ሲሆን የክርስቲያኖች ልዩ መገለጫ ደግሞ መሳሳታቸው ነው።
ተጨማሪ