+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
أَنَّهُ كَانَ يَقُولُ إِذَا أَصْبَحَ: «اللهُمَّ بِكَ أَصْبَحْنَا، وَبِكَ أَمْسَيْنَا، وَبِكَ نَحْيَا، وَبِكَ نَمُوتُ، وَإِلَيْكَ النُّشُورُ» وَإِذَا أَمْسَى قَالَ: «بِكَ أَمْسَيْنَا، وَبِكَ أَصْبَحْنَا، وَبِكَ نَحْيَا، وَبِكَ نَمُوتُ، وَإِلَيْكَ النُّشُورُ» قَالَ: وَمَرَّةً أُخْرَى: «وَإِلَيْكَ الْمَصِيرُ».

[حسن] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي في الكبرى وابن ماجه] - [السنن الكبرى للنسائي: 10323]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና:
እርሳቸው ያነጉ ጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አስበሕና ወቢከ አምሰይና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ በአንተ አነጋን፣ በአንተም አመሸን፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" ያመሹ ጊዜ ደግሞ እንዲህ ይሉ ነበር "አልላሁመ ቢከ አምሰይና ወቢከ አስበሕና ወቢከ ነሕያ ወቢከ ነሙቱ ወኢለይከ ኑሹር" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! በአንተ አመሸሁ፣ በአንተም አነጋሁ፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" በሌላ ጊዜም እንዲህ ብለዋል "… ወኢለይከል መሲር" ትርጉሙም "… መመለሻም ወደ አንተ ነው።"

[ሐሰን ነው።] - - [አስሱነኑል ኩብራ ነሳኢ - 10323]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በርሳቸው ላይ ንጋት የገባ ጊዜ (ይህም ጎህ ከመውጣቱ ጋር የቀኑ መጀመሪያ የሆነው ጊዜ ነው።) እንዲህ ይሉ ነበር:
(አላህ ሆይ! በአንተ አነጋን) በጥበቃህ ተከልለን፣ በፀጋህ ተሸፍነን፣ አንተን በማውሳት ተጠምደን፣ በስምህ ታግዘን፣ በመግጠምህ ተከበን፣ በብልሃትህና በሀይልህ ተንቀሳቃሽ ሆነን አነጋን ማለት ነው። (በአንተ አመሸን፣ በአንተ ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን።) ይህ ማለት ምሽት ላይ ከማድረግ ጋር ቀደም ተብሎ እንደተብራራው እንዲህ ይላል: አላህ ሆይ ባንተ አምሽተናል፣ ህያው አድራጊ በሆነው ስምህ ህያው እንሆናለን። ህይወትን የሚነጥቅ በሚለው ስምህ እንሞታለን። (መቀስቀስም ወዳንተ ነው።) መቀስቀስ ከሞት በኋላ ነው፤ መለያየት ከመሰብሰብ በኋላ ነው። በሁሉም ወቅቶች ሁኔታችን በዚህ ሁኔታ ይቀጥላል። በተቀሩትም ሁኔታዎቼ ከአላህ አልላቀቅምም አልተወውምም።
ከዐስር በኋላ ምሽት የገባ ጊዜም (አላህ ሆይ! በአንተ አመሸሁ፣ በአንተም አነጋሁ፣ በአንተም ህያው እንሆናለን፣ በአንተም እንሞታለን፣ መመለስም ወደ አንተ ነው።) ይሉ ነበር። በዱንያም መመለሻዬ፣ በመጨረሻም መመለሻዬ ወደ አንተ ነው። ህያው የምታደርገኝም አንተው ነህ፤ የምትገድለኝም አንተው ነህ። ማለት ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. በንጋትና ምሽት ወቅት ነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመከተል አኳያ ይህን ዱዓ ማድረግ እንደሚወደድ እንረዳለን።
  2. አንድ ባሪያ በሁሉም ሁኔታዎቹና ወቅቶቹ ወደ ጌታው ፈላጊ መሆኑን እንረዳለን።
  3. ንጋት ላይ አዝካሮችን ለመቅራት በላጩ ወቅት የንጋቱን ጎህ ከወጣችበት ጀምሮ የቀኑ መጀመሪያ ላይ ፀሃይ እስክትወጣ ድረስ፤ የምሽቱን ከዓስር በኋላ ጀምሮ ፀሃይ ከመግባቷ በፊት ድረስ ያለው ወቅት ነው። ከዚህ በኋላ ቢለው ማለትም የንጋቱን ረፋዱ ከፍ ካለ በኋላ ቢለው ይበቃለታል። ከዙህር በኋላ ቢለውም ይበቃለታል። የምሽቱንም ከመጝሪብ በኋላም ቢለው ይህ የዚክር ወቅት ስለሆነ ይበቃለታል።
  4. "መቀስቀስም ወደ አንተ ነው።" የሚለው ንግግር ከንጋት ጋር የሚያገናኘው ይህ ቃል ሰዎች ከሞቱ በኋላና የትንሳኤ ቀን በሚቀሰቀሱ ጊዜ ያለውን ህያው መደረግና ትልቁን መቀስቀስ ስለሚያስታውሰው ነው። ከእንቅልፉ የሚነቃበት ይህ ቀንም ነፍሶች የሚመለሱበትና ሰዎች የሚበተኑበት፣ አላህ የፈጠረው አዲስ ንጋት የሚተነፍስበት አዲስ መቀስቀስና አዲስ ቀን ነው። ይህም አዲስ ንጋት በአደም ልጅ ላይ ምስክር እንዲሆን፣ ወቅቶቹና ሰአቶቹም የስራዎቻችን ድልብ የሚሆኑበት [ሌላ እድል] ነው።
  5. "መመለስም ወደ አንተ ነው።" የሚለው ቃል የምሽት ዚክር ላይ ተስማሚ የሆነው፤ ሰዎች ከስራዎቻቸው፣ ለጥቅማቸውና ለኑሯቸው ከተበታተኑ በኋላ ወደ ቤታቸው በሚመለሱ ጊዜ ወደ የማደሪያቸው መጥተው ማረፍን ያዘወትራሉ። ይህም ወደ አላህ ተባረከ ወተዓላ መመለስን ያስታውሳል።