+ -

عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ رضي الله عنهما أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ كَانَ يَدْعُو بِهَؤُلَاءِ الْكَلِمَاتِ:
«اللَّهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ غَلَبَةِ الدَّيْنِ، وَغَلَبَةِ الْعَدُوِّ، وَشَمَاتَةِ الْأَعْدَاءِ».

[صحيح] - [رواه النسائي وأحمد] - [سنن النسائي: 5475]
المزيــد ...

ከዐብደላህ ቢን ዐምር ቢን ዓስ (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው: የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በነዚህ ቃላቶች ዱዓ ያደርጉ ነበር:
"አላህ ሆይ! እኔ በእዳ ከመሸነፍ፣ በጠላት ከመሸነፍና የጠላቶች ደስታ ምንጭ ከመሆን ባንተ እጠበቃለሁ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ነሳኢና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነኑ ነሳኢይ - 5475]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከነዚህ ጉዳዮች ጥበቃን ፈለጉ:
የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! እኔ በአንተ እጠበቃለሁ) በሌላ በማንም ሳይሆን (በእዳ ከመሸነፍ) ከእዳ ጭንቀት፣ ችግር፤ እዳውን በመክፈልና በመዝጋት ያንተን እገዛ እጠይቅሃለሁ።
ሁለተኛው: (በጠላት ከመሸነፍ) በኔ ላይ ጠላት የበላይ ከመሆንብኝና ከሚቆጣጠረኝ፤ የርሱን ጉዳት መከላከልና በርሱ ላይ ድል መቀናጀትን እጠይቅሃለሁ።
ሶስተኛው: (የጠላቶች የደስታ ምንጭ ከመሆን) ሙስሊሞችን በሚያገኛቸው መከራና ችግር ደስተኛ ከመሆናቸው በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية الرومانية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከእዳና ከመሳሰሉት ከአምልኮ ከሚያጠምዱና ጭንቀትን ከሚያመጡ ነገሮች ሁሉ በአላህ በመጠበቅ ላይ መነሳሳቱን እንረዳለን።
  2. ዕዳ በጥቅሉ ችግር የለውም። ችግር ያለው እዳ መክፈያ በሌለው ሰው ላይ ነው። በእዳ የሚሸነፈውም ይህ ነው።
  3. የሰው ልጅ ጠላትን የሚያስደስትበትንና የሚነወርበትን ነገሮች መራቅ ይገባዋል።
  4. ከሀዲዎች ለአማኞች ያላቸውን ጠላትነትና አማኞች ላይ መከራ መድረሱ የደስታቸው ምንጭ መሆኑ መገለፁን እንረዳለን።
  5. የሰው ልጅ ከደረሰበት መከራ የበለጠ ጠላቶች በመከራው መደሰታቸውን ግልፅ ማድረጋቸው የበለጠ ይጎዳል።