+ -

عَنْ عَبْدِ اللهِ بْنِ عُمَرَ رضي الله عنهما قَالَ: كَانَ مِنْ دُعَاءِ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ:
«اللهُمَّ إِنِّي أَعُوذُ بِكَ مِنْ زَوَالِ نِعْمَتِكَ، وَتَحَوُّلِ عَافِيَتِكَ، وَفُجَاءَةِ نِقْمَتِكَ، وَجَمِيعِ سَخَطِكَ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2739]
المزيــد ...

ከዓብደላህ ቢን ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «ከአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዱዓ መካከል ይህ ዱዓ አንዱ ነበር:
"አላሁመ ኢኒ አዑዙ ቢከ ሚን ዘዋሊ ኒዕመቲክ፣ ወተሐውዉሊ ዓፊየቲክ፣ ወፉጃአቲ ኒቅመቲክ፣ ወጀሚዒ ሰኸጢክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ፣ ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ፣ ከድንገተኛ መከራህ፣ ከአጠቃላይ ቁጣህ በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2739]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከአራት ነገሮች ተጠበቁ:
የመጀመሪያው: (አላህ ሆይ! ፀጋህ ከመወገዱ በአንተ እጠበቃለሁ!) ከሃይማኖታዊም ከአለማዊውም ፀጋህ መወገድ በአንተ እጠበቃለሁ፤ በእስልምና ላይ መፅናትንና ፀጋን የሚያስወግድ ከሆነ ወንጀል ላይ ከመውደቅም መራቅን እጠይቅሃለሁ።
ሁለተኛው: (ለኔ የሰጠኸኝ ደህንነት ከመቀልበስ) ወደ መከራ ከመለወጥ ማለት ነው። ዘውታሪ ደህንነትንና ከሁሉም በሽታዎችና ህመሞች ሰላም መሆንን እጠይቅሃለሁ።
ሶስተኛው: (ከድንገተኛ መከራህ) ከባድ አደጋ ወይም መዐት ማለት ነው። መከራና ቅጣት በድንገት የመጣ ወቅትና ለተውበትና ለመመለስ ጊዜ ከሌለ ለተፈተነበት ሰው መከራው ትልቅና አደገኛ ይሆናል።
አራተኛው: (ከአጠቃላይ ቁጣህ) ለቁጣህ የሚያስገድዱ ከሆኑ ምክንያቶች በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ የተቆጣህበት ሰው በርግጥም ባዶ ቀረ ከሰረ ማለት ነው።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ጠቅላይ የሆኑ ቃላትን የተጠቀሙት የአላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ ቁጣ ምክንያቶች የሆኑትን ንግግሮች፣ ተግባሮችና እምነቶችን በሙሉ እንዲያጠቃልል ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية النيبالية الرومانية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደ አላህ ያላቸውን ፈላጊነት ያስረዳናል።
  2. ይህቺ የተባረከች ዱዓ: ፀጋን ለማመስገን መገጠምንና ወንጀል ላይ ከመውደቅ ጥበቃን መፈለግን ሰብስባ ይዛለች። ወንጀል ላይ መውደቅ ፀጋን ታስወግዳለችና።
  3. የአላህ ቁጣ ምክንያት ከሆኑ ስፍራዎች ለመራቅ መጣር እንደሚገባ እንረዳለን።
  4. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከድንገተኛ መከራ ተጠብቀዋል። ይህም አላህ ባሪያውን የቀጣው ጊዜ እራሱም መከላከል የማይችለውና ፍጡራን ባጠቃላይ ቢሰባሰቡለትም እንኳ የማይችሉት የሆነን መከራን ስለሚያሳርፍበት ነው።
  5. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህ የሰጣቸው ደህንነት ከመቀልበስም ተጠብቀዋል። ይህም አላህ በደህንነቱ እርሳቸውን ከመረጣቸው የሁለቱንም አለም መልካም ተጎናፀፉ፤ የአላህ ደህንነት ከተቀለበሰ ደግሞ የሁለቱም ሀገር ጉዳት የሚደርስባቸው ስለሆነ ነው። የዚህ አለም ደህንነት ለዲንም ሆነ ለዱንያ መስተካከል ምክንያት ስለሆነ ነው።