+ -

عَنْ عَائِشَةَ أُمِّ المُؤْمِنينَ رضي الله عنها أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَلَّمَهَا هَذَا الدُّعَاءَ:
«اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنْ الْخَيْرِ كُلِّهِ، عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ، مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ الشَّرِّ كُلِّهِ، عَاجِلِهِ وَآجِلِهِ، مَا عَلِمْتُ مِنْهُ وَمَا لَمْ أَعْلَمْ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ مِنْ خَيْرِ مَا سَأَلَكَ عَبْدُكَ وَنَبِيُّكَ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ شَرِّ مَا عَاذَ بِهِ عَبْدُكَ وَنَبِيُّكَ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْجَنَّةَ، وَمَا قَرَّبَ إِلَيْهَا مِنْ قَوْلٍ أَوْ عَمَلٍ، وَأَعُوذُ بِكَ مِنْ النَّارِ، وَمَا قَرَّبَ إِلَيْهَا مِنْ قَوْلٍ أَوْ عَمَلٍ، وَأَسْأَلُكَ أَنْ تَجْعَلَ كُلَّ قَضَاءٍ قَضَيْتَهُ لِي خَيْرًا».

[صحيح] - [رواه ابن ماجه وأحمد] - [سنن ابن ماجه: 3846]
المزيــد ...

የአማኞች እናት ከሆነችው ከዓኢሻ (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና - እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ይህን ዱዓ አስተማሯት:
"አልላሁመ ኢኒ አስአሉከ ሚነል ኸይሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወአጂሊህ፣ ማ ዓሊምቱ ሚንሁ ወማለም አዕለም፣ ወአዑዙ ቢከ ሚነ ሸሪ ኩሊህ፣ ዓጂሊሂ ወአጂሊህ ማዓሊምቱ ሚንሁ ወማለም አዕለም። አላሁመ ኢኒ አስአሉከ ሚን ኸይሪ ማሰአለከ ዐብዱከ ወነቢዩከ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ ማዓዘ ቢሂ ዐብዱከ ወነቢዩክ፣ አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ጀነተ ወማ ቀረበ ኢለይሃ ሚን ቀውሊን አው ዓመሊን፣ ወአስአሉከ አንተጅዐለ ኩለ ቀዿኢን ቀደይተሁ ሊ ኸይራ" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ሁሉንም እጠይቅሃለሁ፤ ከመጥፎ ነገርም ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ከሁሉም መጥፎ ነገር ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ባሪያህና ነቢይህ የጠየቀህን መልካም ነገር እጠይቅሃለሁ፣ ባሪያህና ነቢይህ ከተጠበቁት መጥፎ ነገርም ባንተ እጠበቃለሁ። አላህ ሆይ! ጀነትንና ወደርሷ የሚያቃርብን ንግግር ወይም ተግባር እጠይቅሃለሁ። ከእሳትና ወደርሷ ከሚያቀርቡ ንግግሮችና ተግባሮች ባንተ እጠበቃለሁ። ለኔ የወሰንከውን ሁሉንም ውሳኔዎች መልካም እንድታደርግልኝም እጠይቅሃለሁ።" ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።] - - [ሱነን ኢብኑ ማጀህ - 3846]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዓኢሻን (ረዲየሏሁ ዐንሃ) - አላህ መልካም ሥራዋን ይውደድላትና ጠቅላይ ዱዓዎችን አስተማሯት። እነርሱም እነዚህ አራት ዱዓዎች ናቸው:
የመጀመሪያው: ሁሉንም መልካም ነገር የጠቀለለ ዱዓ ነው (አላህ ሆይ! እኔ ከመልካም ነገር ሁሉንም እጠይቅሃለሁ) አጠቃላዩን (ቅርቡንም) ወቅቱ የቀረበውን (የዘገየውንም) መምጫ ወቅቱ የራቀውንም (ከርሱ ያወቅኩትንም) ካሳወቅከኝም (ያላወቅኩትንም) ከአንተ እውቀት ብቻ ከሆነውም እጠይቅሃለሁ። በዚህም ነገሮችን አዋቂና ውስጠ አዋቂ ወደሆነው አላህ ብቻ ማስጠጋት አለበት። ይህንን ዱዓ ላደረገ ሙስሊም አሏህ በላጩንና የተሻለውን ይመርጥለታል። (ከመጥፎ ነገርም ቅርቡንም የዘገየውንም፣ ከርሱ ያወቅኩትንም ያላወቅኩትንም ከሁሉም ነገር) (መጠበቂያዬ) መጠጊያዬ አንተው ነህ።
ሁለተኛው ዱዓ: አንድ ሙስሊም በዱዓው ወሰን ከማለፍ ጥበቃን የሚጠይቅበት ነው። (ባሪያህና ነቢይህ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የጠየቀህን መልካም ነገር) (አላህ ሆይ እኔ እጠይቅሃለሁ) ከአንተ እፈልጋለሁ። (ባሪያህና ነቢይህ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተጠበቁት መጥፎ ነገርም) (ባንተ እጠበቃለሁ) እጠጋለሁ። በዚህ ዱዓ ጠያቂው ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የለመኑትን የዱዓ አይነቶች ሳይቆጥር እርሳቸው (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና አላህን ከለመኑትና ከርሱ ከፈለጉት የተሻለውን እንዲሰጠው እየጠየቀ ነው።
ሶስተኛው ዱዓ: ጀነት መግባትና ከእሳት መራቅን መፈለግ ነው። ይህም የሁሉም ሙስሊም ፍላጎትና የስራው ግብ ነው። (አላህ ሆይ! ጀነትን) በርሷ መጎናፀፍን (ወደርሷ የሚያቃርብን ንግግር ወይም ተግባርን እጠይቅሃለሁ።) የሚያስደስትህን መልካም ስራ እጠይቅሃለሁ። (ከእሳትም በአንተ እጠበቃለሁ።) በአንተ እዝነት ካልሆነ በቀር ከፀያፍ ተግባር መጠበቂያ የለምና። (ወደርሷ ከሚያቃርብን ንግግር ወይም ተግባርም በአንተ እጠበቃለሁ።) ከሚያስቆጣህ ወንጀል በአንተ እጠበቃለሁ ማለት ነው።
አራተኛው ዱዓ: በአላህ ውሳኔ የመውደድ ዱዓ ነው። (ለኔ የወሰንከውን ሁሉንም ውሳኔዎች መልካም እንድታደርግልኝ እጠይቅሃለሁ።) አላህ ለኔ የወሰነውን ነገር ሁሉ ለኔ መልካም እንዲያደርግልኝ እጠይቃለሁ። ይህም በአላህ ፍርድ የመውደድ ዱዓ ነው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዓኢሻን እንዳስተማሯት አንድ ሰው ለቤተሰቦቹ ጠቃሚ የሆኑን የዲንና የዱንያ ጉዳዮችን ማስተማር እንደሚገባው እንረዳለን።
  2. ለአንድ ሙስሊም በላጩ ከነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና የመጡ ዱዓዎችን መሸምደድ ነው። ይህም ጠቅላይ ከሆኑ ዱዓዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ነው።
  3. ዑለማዎች ስለዚህ ሐዲሥ እንዲህ ብለዋል: ይህ ሐዲሥ መልካምን በመጠየቅና ከመጥፎ በመጠበቅ ረገድ ጠቅላይ ሐዲሥ ነው። ይህ ሐዲሥ ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ከተሰጣቸው ጠቅላይ ንግግር መካከልም ነው።
  4. ከአላህ እዝነት ቀጥሎ ጀነት ከሚያስገቡ ምክንያቶች መካከል መልካም ተግባራትና ንግግሮች ይጠቀሳሉ።