+ -

عَنِ ابنِ عُمَرَ رضي الله عنهما قَالَ:
لَمْ يَكُنْ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَدَعُ هَؤُلَاءِ الدَّعَوَاتِ، حِينَ يُمْسِي وَحِينَ يُصْبِحُ: «اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَافِيَةَ فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ، اللَّهُمَّ إِنِّي أَسْأَلُكَ الْعَفْوَ وَالْعَافِيَةَ فِي دِينِي وَدُنْيَايَ وَأَهْلِي وَمَالِي، اللَّهُمَّ اسْتُرْ عَوْرَتِي -أَو: عَوْرَاتِي- وَآمِنْ رَوْعَاتِي، اللَّهُمَّ احْفَظْنِي مِنْ بَيْنِ يَدَيَّ، وَمِنْ خَلْفِي، وَعَنْ يَمِينِي، وَعَنْ شِمَالِي، وَمِنْ فَوْقِي، وَأَعُوذُ بِعَظَمَتِكَ أَنْ أُغْتَالَ مِنْ تَحْتِي».

[صحيح] - [رواه أبو داود والنسائي وابن ماجه وأحمد] - [سنن أبي داود: 5074]
المزيــد ...

ከኢብኑ ዑመር (ረዲየሏሁ ዐንሁማ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
«የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሚያመሹና በሚያነጉ ጊዜ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይቦዝኑም ነበር። "አላሁም ኢኒ አስአሉከልዓፊያተ ፊድ-ዱንያ ወልአኺረቲ፣ አላሁም ኢኒ አስአሉከል ዐፍወ ወልዓፊየተ ፊ ዲኒ ወዱንያየ ወአህሊ ወማሊ፣ አላሁም ስቱር ዐውረቲ -አው ዓውራቲ- ወአሚን ረውዓቲ፣ አሏሁም ሕፈዝኒ ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ፣ ወአዑዙ ቢአዞመቲክ 'አን ኡግታለ ሚን ተሕቲ"» ትርጉሙም (አላህ ሆይ! በዱንያም ሆነ በመጪው አለም ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ በዱንያዬ፣ በመጪው አለሜ፣ በቤተሰቤና ገንዘቤ ይቅርታህንና ደህንነትን እጠይቅሃለሁ፤ አላህ ሆይ ነውሬን ወይም ነውሮቼን ሸሽግልኝ፣ ከፍርሃቴም ደህንነትን ስጠኝ፤ አላህ ሆይ! ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም ጠብቀኝ! ከበታቼ ድንገታዊ ጥቃት ከሚደርስብኝም በልቅናህ እጠበቃለሁ።) ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ ነሳኢ፣ ኢብኑማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 5074]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ሲመሽና ሲነጋ እነዚህን ዱዓዎች ከማድረግ አይቦዝኑም ነበር።
(አላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዓፊየተ) አላህ ሆይ! ከአለማዊ በሽታዎች፣ መከራዎችና ችግሮች፣ ከዲናዊ ፈተናዎችና ዝንባሌዎች ሰላም መሆንን (ፊድዱንያ ወልአኺረተ) በቅርቡም ሆነ በመጪው አለም እጠይቅሃለሁ።
(አልላሁመ ኢኒ አስአሉከል ዐፍው) አላህ ሆይ! ወንጀሎቼን ማበስ፣ ይቅር ማለትህን (ወልዓፊየተ) ከነውር መፅዳትን (ፊዲኒ) በሃይማኖቴ ከሽርክ፣ ከቢድዓና ከወንጀሎች፤ (ወዱንያየ) በዓለማዊ ህይወቴ ደሞ ከመከራዎች፣ ከሚያውክና ከክፋቶች (ወአህሊ) በቤተሰቤ ላይ በባለቤቴ፣ በልጆቼና ቅርብ ዘመዶቼ (ወማሊ) በገንዘቤና በስራዬ ላይ ደህና መሆንን እጠይቅሃለሁ።
(አልላሁመስቱር ዐውራቲ) አላህ ሆይ! እኔ ላይ ያሉትን ነውሮች፣ ጉድለቶች፣ እንከኖችን ሸሽገኝ፤ ወንጀሌንም አብስ። (ወአሚን ረውዓቲ) ድንጋጤዬንና ፍርሃቴን ደህንነት ስጠው።
(አልላሁመሕፈዝኒ) አላህ ሆይ! የሚያውኩኝንና መከራዎችን ከኔ አስወግድልኝ። (ሚን በይኒ የደየ፣ ወሚን ኸልፊ፣ ወዓን የሚኒ፣ ወዓን ሺማሊ፣ ወሚን ፈውቂ) (ከፊት ለፊቴም፣ ከኋላዬም፣ ከቀኜም፣ ከግራዬም፣ ከበላዬም) በዚህም አላህ ከሁሉም አቅጣጫዎች እንዲጠብቃቸው ጠየቁ። መከራዎችና መአቶች ወደ ሰው የሚመጡትና የሚዞሩት ከነዚህ አቅጣጫዎች መካከል በአንዱ ነውና።
(ወአዑዙ ቢዐዞመቲከ አንኡግታል) በድንገት ከመያዝና ተዘናግቼ ከምጠፋ በልቅናህ እጠበቃለሁ። (ሚንተሕቲ) በመሬት መደርመስ ከመጥፋትም ባንተ እጠበቃለሁ።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ስዋሒልኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. መልክተኛውን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በመከተል እነዚህን ቃላቶች መጠባበቅ እንደሚገባ እንረዳለን።
  2. የሰው ልጅ የሃይማኖቱን ደህንነት አላህን እንዲጠይቅ እንደታዘዘው ሁሉ ለዓለማዊ ጉዳዩም እንዲጠይቅ ታዟል።
  3. ጢቢ እንዲህ ብለዋል: «ስድስቱን አቅጣጫዎች ማጠቃለላቸው የመከራዎች መምጣት በነርሱ በኩል ስለሆነ ነው። የታች አቅጣጫን አበክረው የጠቀሱት ከታች የሚመጣ መከራ አዋራጅ ስለሆነ ነው።»
  4. ንጋት ላይ አዝካሮችን ለመቅራት በላጩ ወቅት: ጎህ ከወጣ ጀምሮ የቀኑ መጀመሪያ ላይ ፀሃይ እስክትወጣ ድረስና ከዐስር በኋላ ፀሃይ እስክትገባ ድረስ ነው። ከዚህ በኋላም ቢል ማለትም ረፋዱ ከፍ ካለ በኋላም ቢል ይበቃለታል። ከዙህር በኋላም ቢል ይበቃለታል። ከመጝሪብ በኋላም ቢል ይበቃለታል። ይህም የዚክር ወቅት ነውና።
  5. ዚክሩ መባል ያለበት በተለየ ወቅት እንደሆነ ማስረጃ ከጠቆመ የሱረቱል በቀራ መጨረሻ ሁለት አንቀጾችን ምሽት ላይ መቅራትን ይመስል ፀሃይ ከገባ በኋላ ምሽት ላይ ነው የሚፈፀመው።