عَنِ أَبِي مُوسَى رضي الله عنه، عَنِ النَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَنَّهُ كَانَ يَدْعُو بِهَذَا الدُّعَاءِ:
«رَبِّ اغْفِرْ لِي خَطِيئَتِي وَجَهْلِي، وَإِسْرَافِي فِي أَمْرِي كُلِّهِ، وَمَا أَنْتَ أَعْلَمُ بِهِ مِنِّي، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي خَطَايَايَ، وَعَمْدِي وَجَهْلِي وَهَزْلِي، وَكُلُّ ذَلِكَ عِنْدِي، اللَّهُمَّ اغْفِرْ لِي مَا قَدَّمْتُ وَمَا أَخَّرْتُ، وَمَا أَسْرَرْتُ وَمَا أَعْلَنْتُ، أَنْتَ المُقَدِّمُ وَأَنْتَ المُؤَخِّرُ، وَأَنْتَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 6398]
المزيــد ...
ከአቡ ሙሳ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እነዚህን ዱዓዎች ያደርጉ ነበር:
"ረቢግፊርሊ ኸጢአቲ፣ ወጀህሊ፣ ወኢስራፊ ፊ አምሪ ኩሊህ፣ ወማ አንተ አዕለሙ ቢሂ ሚኒ፣ አላሁምመግፊርሊ ኸጧያየ፣ ወዓምዲ፣ ወጀህሊ፣ ወሀዝሊ ወኩሉ ዛሊከ ዒንዲ፤ አላሁመግፊርሊ ማ ቀደምቱ፣ ወማ አኸርቱ፣ ወማ አስረርቱ፣ ወማ አዕለንቱ፤ አንተል ሙቀዲሙ፣ ወአንተል ሙአኺሩ፣ ወአንተ ዐላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ትርጉሙም "ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን፣ አለማወቄን፣ በሁሉም ነገር ወሰን ማለፌን፣ አንተ ከኔ የበለጠ የምታውቀውንም ማረኝ። አላህ ሆይ! ወንጀሌን፣ ሆን ብዬ የሰራሁትን፣ አለማወቄን፣ ቀልዴን ማረኝ፤ ይህ ሁሉም ከኔው ነው። አላህ ሆይ! ያስቀደምኩትን፣ ያዘገየሁትን፣ የመሰጠርኩትን፣ ግልፅ ያወጣሁትን ወንጀል ማረኝ፤ አንተ አስቀዳሚ ነህ፣ አንተም የሚያዘገይ ነህ፣ አንተም በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ።" ማለት ነው።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6398]
ጠቅላይ ከሆኑት የነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዱዓዎች መካከል ይህ አንዱ ነበር:
"ጌታዬ ሆይ! ወንጀሌን ማረኝ" ሀጢዐቴን "አለማወቄንም" ያለ እውቀት ከኔ የተከሰተውንም ወንጀል ማረኝ።
"በሁሉም ነገሬ ወሰን ማለፌንም" ከልክ ማለፌንም ማጓደሌንም ማረኝ።
"አንተ ከኔ የበለጠ የምታውቀውንም ማረኝ።" አንተ አውቀኸው እኔ የረሳሁትን ማለት ነው።
"አላህ ሆይ! ወንጀሌንና ሆን ብዬ የሰራሁትን ማረኝ" ወንጀልነቱን አውቄና ሆን ብዬ የሰራሁትንም ማረኝ።
"ምሬንም ቀልዴንም" በቀልድ የሰራሁትንም በሁለቱም ሁኔታ ላይ ሆኜ የሰራሁትንም ማረኝ።
"ይህ ሁሉ ከኔ ነው።" የተጠቀሱት ወንጀሎችና ነውሮች ቢሰበሰቡ ከኔው ናቸው።
"አላህ ሆይ! ያስቀደምኩትን ወንጀል ማረኝ!" ያለፈውን "ያዘገየሁትንም ማረኝ" ለወደፊት የምሰራውን ማረኝ።
"የመሰጠርኩትንም" የደበቅኩትን "ግልፅ ያወጣሁትንም" ይፋ ያወጣሁትን ማረኝ።
"አንተ አስቀዳሚ ነህ! አንተም የሚያዘገይ ነህ!" ከፍጥረትህ የፈለግከውን ወደ እዝነትህ በመግጠምህም ለምትወደው ነገር ታስቀድማለህ። አንተ የፈለግከውንም ሰው እርሱን በማዋረድ ከነዚህ ነገሮች ታዘገየዋለህ። ከነገሮች ያዘገየኸውን የሚየስቀድም፣ ያስቀደምከውንም የሚያዘገይ የለም።
"አንተ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነህ።" ችሎታው የተሟላ፣ ፍላጎቱ የተሟላ፣ ለምትሻው ነገር ሁሉ ፈፃሚ ነህ ማለት ነው።