+ -

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رضي الله عنه قَالَ: كَانَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ يَقُولُ:
«اللهُمَّ أَصْلِحْ لِي دِينِي الَّذِي هُوَ عِصْمَةُ أَمْرِي، وَأَصْلِحْ لِي دُنْيَايَ الَّتِي فِيهَا مَعَاشِي، وَأَصْلِحْ لِي آخِرَتِي الَّتِي فِيهَا مَعَادِي، وَاجْعَلِ الْحَيَاةَ زِيَادَةً لِي فِي كُلِّ خَيْرٍ، وَاجْعَلِ الْمَوْتَ رَاحَةً لِي مِنْ كُلِّ شَرٍّ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 2720]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ (ረዲየሏሁ ዐንሁ) - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: «የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንዲህ ይሉ ነበር:
"አልላሁመ አስሊሕ ሊ ዲኒለዚ ሁወ ዒስመቱ አምሪ ወአስሊሕ ሊ ዱንያየለቲ ፊሃ መዓሺ፣ ወአስሊሕ ሊ አኺረቲለቲ ፊሃ መዓዲ፣ ወጅዐሊል ሐያተ ዚያደተን ሊ ፊ ኩሊ ኸይር፣ ወጅዐሊል መውተ ራሐተን ሊ ሚን ኩሊ ሸር"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! የነገሮቼ መጠበቂያ የሆነውን ሃይማኖቴን አስተካክልልኝ። በውስጧ ኑሮዬ የሆነውን ዱንያዬንም አስተካክልልኝ። መመለሻዬ የሆነውን የመጨረሻውን አለምም አስተካክልልኝ። ህይወቴን ሁሉንም መልካም ነገር የምጨምርበት አድርገው። ሞቴንም ከሁሉም መጥፎ ነገር የማርፍበት አድርገው።" ማለት ነው።

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 2720]

ትንታኔ

ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ለመሙላት የተላኩለት የሆነውን የመልካም ስነምግባር መሰረቶችን የሰበሰበች ዱዓ አደረጉ። እነርሱም: የሃይማኖት፣ የዱንያና የመጨረሻው አለም መስተካከል ናቸው። በነዚህ አጠር ባሉ ቃላቶች የነዚህን ሶስቱንም ያጠቃለለ ጥቅምን አከታትለው ለመኑ። በቅድሚያ በሃይማኖት መስተካከል ጀመሩ። የሁለቱም ሀገሮች ሁኔታ የሚስተካከሉት በርሱ ነውና። እንዲህ አሉ:
(አላህ ሆይ! ሃይማኖቴን አስተካክለው።) በተሟላ መልኩ ስነስርዓቱን ጠብቄ እንድቆም ወፍቀኝ (አሳካልኝ)
(የነገሮቼ መጠበቂያ የሆነውን) የጉዳዮቼ ባጠቃላይ ጠባቂ የሆነውን ሃይማኖቴ ከተበላሸ ጉዳዮቼ ባጠቃላይ ይበላሻል፤ ባዶዬን እቀራለሁ፣ እከስራለሁ። እንዲስተካከል የተፈለገው የሃይማኖት ጉዳይም ዱንያ ስትስተካከል ካልሆነ በቀር ስለማይስተካከል እንዲህ አሉ:
(ዱንያዬን ለኔ አስተካክልልኝ) የሰውነት ጤና፣ ደህንነት፣ ሲሳይ፣ መልካም ሚስት፣ ጥሩ ዘር፣ ሐላል የሆነና አንተን ለማምለክ የሚያግዘኝን የሚያሰፈልገኝን በመስጠት (ዱንያዬን ለኔ አስተካክልልኝ) ቀጥለው ዱንያቸው እንዲስተካከል የጠየቁበትን ምክንያት እንዲህ በማለት ጠየቁ:
(በውስጧ ኑሮዬ የሆነውን) የኑሮዬና የህይወት ዘመኔ ስፍራ የሆነውን።
(መመለሻዬ የሆነውን የመጨረሻውን አለም አስተካክልልኝ።) አንተን ለመገናኘት የምመለስበት የሆነውን ማለት ነው። መጨረሻ የሚያምረውም ስራን በማስተካከልና አላህ ባሪያውን ለአምልኮ፣ ለኢኽላስና ለመልካም ፍፃሜ በመግጠሙ ነው።
ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና መጪው አለምን ከዱንያ በኋላ ያስከተሉት የመጀመሪያው አለም ለሁለተኛው አለም መስተካከል መዳረሻ ስለሆነ ነው። ዱኒያው አላህ በፈለገው መልኩ የተስተካከለለት ሰው መጪው አለምም ለርሱ ይስተካከልለታል በርሷም ውስጥ ይደሰታል።
(ህይወቴን አድርግ) የእድሜዬ መርዘምን (በሁሉም በኩል መልካም ነገር የምጨምርበት) መልካም ስራን የማበዛበት (ሞቴን አድርገው) መፍጠኑን (ከሁሉም መጥፎ ነገር የማርፍበት) ሞትን ከፈተናዎች፣ ከመከራ፣ የወንጀልና የዝንጉነት ፈተና ላይ ከመውደቅ፣ ከዱንያ ችግርና ጭንቀት የምገላገልበትና እረፍትን የማገኝበት አድርገው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ስዋሒልኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية الرومانية Oromisht
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ዲን ወሳኝ ነገር ነው። ስለዚህም ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዱዓቸውን ከርሱ ጀመሩ።
  2. ዲን ለሰው ልጅ ሁሉንም መጥፎ ነገር የሚከላከልለት መጠበቂያው ነው።
  3. በዱኒያዊ ጉዳዮች ዱዓ የሚደረገው ዲንና መጪው አለም እንዲስተካከል ነው።
  4. የዲን ፈተና በመፍራት ሞትን መመኘት ወይም አላህ ሸሂድ አድርጎ እንዲገድለው መጠየቅ አይጠላም።