የሓዲሦች ዝርዝር

1. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ጫማ ሲለብሱ፣ ሲያበጥሩ፣ ሲፅዳዱና በሁሉም ጉዳያቸው ቀኝን መጠቀም ይወዱ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
2. የነቢዩን (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና እንጥላቸውን እስክመለከት ድረስ በጭራሽ ሙሉ አፋቸውን ከፍተው ሲስቁ ተመልክቻቸው አላውቅም። ሲስቁ ፈገግ ብቻ ነበር የሚሉት - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
3. አንዳችሁ የሚወደውን ህልም በተመለከተ ጊዜ እርሷ ከአላህ ናትና በርሷ ምክንያት አላህን ያመስግንም ለሌሎችም ያውራት፤ ከዚህ ውጪ የሚጠላውን ህልም የተመለከተ ጊዜ ደሞ እርሷ ከሸይጧን ናትና ከክፋቷ በአላህ ይጠበቅ፤ ለአንድም ሰው አያውራ። እርሷም አትጎዳውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
4. ሁለት ሴት ልጆችን እስኪደርሱ ድረስ የተንከባከበ ሰው የትንሳኤ ቀን እኔና እሱ እንዲህ ሆነን ይመጣል።" ጣታቸውንም አጣበቁ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
5. በአማኞች ላይ ወይም በኡመቴ ላይ እንዳይከብዳቸው ብዬ ነው እንጂ በሁሉም ሶላቶች ወቅት መፋቂያ እንዲጠቀሙ አዛቸው ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
6. ባሮች የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መልዐክ ወርደው እንዲህ የሚሉበት ቢሆን እንጂ፤ አንደኛቸው: "አላህ ሆይ! ለሰጪ ምትኩን ስጠው!" ሲል ሌላኛቸው ደግሞ "አላህ ሆይ! ለቋጣሪ ጥፋትን ስጠው!" ይላል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
7. ሚዛናዊ ሁኑ፤ በተቻለ መጠን ወደ እሱ ቅርብ ለመሆን ሞክሩ ከናንተ መካከል አንድም ሰው በስራው እንደማይድንም እወቁ!" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርሶም ቢሆኑ በስራዎት አይድኑምን?" አሉ። እርሳቸውም "አላህ ከርሱ በሆነ እዝነትና ችሮታ ካልሸፈነኝ በቀር እኔም ብሆን በስራዬ አልድንም።" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
8. አላሁመ አዑዙ ቢሪዷከ ሚን ሰኸጢክ፣ ወቢሙዓፋቲከ ሚን ዑቁበቲክ፣ ወአዑዙ ቢከ ሚንክ፣ ላኡሕሲ ሠናአን ዐለይክ አንተ ከማ አሥነይተ ዐላ ነፍሲክ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ከቁጣህ በውዴታህ፣ ከቅጣትህ በይቅር ባይነትህ እጠበቃለሁ፤ ከአንተ በአንተ እጠበቃለሁ፤ አንተ እራስህን ያወደስከውን ያህል ላወድስህ አልችልም።" ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
9. የጀነት ነዋሪ ማን እንደሆነ አልነግራችሁምን? ደካማ፣ ዝቅ የሚደረግ፣ በአላህ ላይ ቢምል ግን አላህ መሃላውን እውን የሚያደርግለት የሆነ ሁሉ ነው። የእሳት ነዋሪስ ማን እንደሆነ አልነግራችሁምን? ልበ ደረቅ፣ ትዕቢተኛና በኩራት የተሞላ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
10. እኔ አንዲት ንግግር አውቃለሁ። እርሷን ቢናገራት አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል። አዑዙ ቢላሂ ሚነሽሸይጧን ቢል አሁን እየተሰማው ያለው ስሜት ይወገድለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
11. መልካም ህልም ከአላህ ነው። መጥፎ ህልም ከሸይጧን ነው። አንዳችሁ የሚፈራውን መጥፎ ህልም የተመለከተ ጊዜ ወደ ግራው ይትፋ፤ ከህልሙ ክፋትም በአላህ ይጠበቅ። ያኔ እርሷም አትጎዳውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
12. የአላህ መልክተኛ ሆይ! መዳኛ ምንድን ነው? አልኳቸው። እርሳቸውም "ምላስህን ተቆጣጠር፤ ቤትህ ይስፋህ፤ በወንጀልህም ላይ አልቅስ!" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
13. እኔ ባሪያዬ ባሰበኝ በኩል ነኝ። ባስታወሰኝም ጊዜ እኔ ከርሱ ጋር ነኝ። - 4 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
14. እናታችን ዓኢሻን እንዲህ ብየ ጠየቅኳት: "ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ቤታቸው የገቡ ጊዜ በምን ነበር የሚጀምሩት?" እርሷም "በመፋቅ" በማለት መለሰችልኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
15. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ዘንድ እስኪነጋ ድረስ ምሽቱን የተኛ ሰውዬ ተወሳ። እርሳቸውም "ይህ ሸይጧን ጆሮዎቹ ውስጥ ወይም ጆሮው ውስጥ የሸናበት ሰው ነው።" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
16. የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና በሌላ ጊዜያት ለአምልኮ ከሚጥሩት የተለየ በመጨረሻዎቹ አስሩ የረመዷን ቀናት ይጥሩ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
17. አንድ ባሪያ የአንድን ባሪያ ነውር በዱንያ አይሸፍንም፤ የትንሳኤ ቀን አላህ ነውሩን የሚሸፍንለት ቢሆን እንጂ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
18. አንዳችሁ በአላህ ላይ ያለውን እሳቤ ሳያሳምር እንዳይሞት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
19. እንዳልከው ከሆነ አንተ ትኩስ አመድ እያቃምካቸው ነው። በዚህ ሁኔታ ላይ እስከዘወተርክ ድረስም ከአላህ የሆነ አጋዥ ከአንተ ጋር አይወገድም።" አሉት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
20. በአላህ መንገድ ሲታገሉ አቧራ የለበሱ እግሮችን እሳት ልትነካቸው አትችልም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
21. ሰዎች በውስጧ አላህን ያላወሱበትን መሰባሰብን (ጨርሰው) አይነሱም። የአህያ ሬሳ (በልተው) እንደሚሄዱ እና (በስብሰባው አላህን ባለማውሳታቸው) በእነርሱ ላይ ጸጸት (ቁጭትን) ቢሆንባቸው እንጂ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
22. ጌታውን የሚያወሳና የማያወሳ ሰው ምሳሌ እንደ ህያውና እንደ ሞተ ሰው ምሳሌ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
23. ከኔ በኋላ በናንተ ላይ ከምፈራላችሁ ነገሮች መካከል በናንተ ላይ የሚከፈትላችሁን የዱንያ ጌጥና ውበት ነው። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
24. ‹‹ከትንሳኤ ቀን ችግሮች አላህ እንዲገላግለው ያስደሰተው ሰው ለችግርተኛ ፋታ ይስጥ ወይም ከርሱ ያቅልልለት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
25. ከጀሀነም ነዋሪዎች መካከል እጅግ ዝቅተኛ ቅጣት የሚቀጣው ለርሱ ሁለት የእሳት ጫማዎችና የጫማ ማሰሪያዎች የሚደረግለት ነው። በነርሱም ምክንያት ድስጥ እንደሚንፈቀፈቀው አንጎሉ ይንፈቀፈቃል። ከርሱ የበለጠ ቅጣት የሚቀጣ አንድም ሰው አለ ብሎም አያስብም። እርሱ እየተቀጣ ያለው ግን እጅግ ዝቅተኛውን ቅጣት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
26. ‹አንድ አማኝ የትንሳኤ ቀን ወደ ጌታው ይቀርባል። በርሱ ላይ መሸፈኛውን አኑሮበት ወንጀሎቹን እንዲያምን ያደርገዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
27. በጎ ተግባር ማለት መልካም ስነምግባር ነው። ወንጀል ማለት በልብህ ውስጥ የተጣረጠርከውና (የተመላለሰ) ሰዎች ማወቃቸውን የጠላኸው ነገር ነው።" አሉኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
28. እነዚህን ሁለት ጫማዎቼን ያዝና ሂድ! ከዚህ የአትክልት ግቢ ውጪ የምታገኘውን ላኢላሃ ኢለሏህን ከልቡ አምኖበት የሚመሰክርን ሰው በጀነት አበስረው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
29. ቁርአንን አሳምሮ የሚያነብ ሰው የተከበሩና ታዛዥ ከሆኑ መላዕክቶች ጋር ነው፤ ቁርኣንን ሲያነብ ከብዶት እየተቸገረ የሚያነብ ሰው ደሞ ለርሱ ሁለት ምንዳ አለው። - 10 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
30. የአላህ መልክተኛ -የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- በሶስት ወቅቶች ላይ ከመስገድ ወይም ሟቾቻችንን ከመቅበር ይከለክሉን ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
31. ሰዎች ሶላታቸው ውስጥ ሆነው ዓይኖቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ የሚያደርጉት ምን ሆነው ነው!?" በዚህ ዙሪያም አጠንክረው አስጠነቀቁ። እንዲህም አሉ "ከዚህ ተግባራቸው ይከልከሉ ወይም አይናቸው ትነጠቃለች።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
32. በድርና ሑደይቢያ ላይ የተሳተፈ ሰው እሳት አይገባም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
33. አንዳችሁ የሞተ ጊዜ ለርሱ ጧትም ማታም ማረፊያው ይቀርብለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
34. አንዳችሁ ለብቻው የሚሰግደውን ሶላት የህብረት ሶላት በሃያ አምስት ክፍል (እጥፍ) ይበልጠዋል። የምሽት መልአክቶችና የቀን መልአክቶች በፈጅር ሶላት ወቅት ይገናኛሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
35. ነቢዩ ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም -የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና- ፀጉር የምትቀጥልን፣ የምታስቀጥልን፣ የምትነቅስንና የምታስነቅስን ረግመዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
36. ከሶስት ዓይነት አካላት ላይ ብእር ተነስቷል። የተኛ ሰው እስኪነቃ ድረስ፤ ህፃን ልጅ አቅመ አዳም እስኪደርስ ድረስ እና እብድ ጤነኛ እስኪሆን ድረስ ነው። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
37. በአላህ መንገድ ላይ አንድ ቀን የጾመ ሰው አላህ ፊቱን ከእሳት ሰባ ዓመታት ያርቀዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
38. ሰዎች ማፍጠርን እስካቻኮሉ ድረስ መልካም ላይ ከመሆን አይወገዱም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
39. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) በመካከላችን ሳሉ ዘካተል ፊጥርን ለሁሉም ህፃንና አዋቂ፣ ነፃም ሆነ ወይም ባሪያ አንድ ቁና ከስንዴ ወይም አንድ ቁና የደረቀ ወተት (እርጎ) ወይም አንድ ቁና ከገብስ ወይም አንድ ቁና ከተምር ወይም አንድ ቁና ከዘቢብ እናወጣ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
40. ከነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጋር ሰሑር በላን። ከዚያም ወደ ሶላት ቆሙ። እኔም (አነስም ለዘይድ) "በአዛንና በሰሑር መካከል ምን ያክል ወቅት ነበር?" አልኩኝ። እርሱም (ዘይድም)፦ "ሃምሳ አንቀፅ የሚቀራበት ያህል" አለኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
41. ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) አላህ ህይወታቸውን እስከወሰደባት ጊዜ ድረስ የረመዷን የመጨረሻዎቹ አስር ቀናቶችን ኢዕቲካፍ ያደርጉ ነበር። ከዚያም ከርሳቸው ህልፈት በኋላ ባለቤቶቻቸው ኢዕቲካፍ አድርገዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
42. ሰሑር ተመገቡ! በሰሑር ውስጥ በረከት አለ። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
43. ከረመዷን አንድ ቀንም ሆነ ሁለት ቀን በፊት ቀድማቹህ አትፁሙ። ነገር ግን ያስለመደው ጾም የነበረበት ሰው ከሆነ ይፁመው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
44. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ላይ ይስፈንና ዘካተል ፊጥርን አንድ ቁና ከተምር ወይም አንድ ቁና ከገብስ ማውጣትን በባሪያውም፣ በነፃውም፣ በወንዱም፣ በሴቱም፣ በህፃኑም፣ በትልቁም ሙስሊም ላይ ግዴታ አደረጉ። ሰዎች ወደ ሶላት ከመውጣታቸው በፊት እንድትሰጥም አዘዙ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
45. አንድ ሙስሊም ሴት የአንድ ምሽት መንገድ ከርሷ ጋር የዝምድና ባለቤት የሆነ ወንድ ከሌለ በቀር ልትጓዝ አልተፈቀደላትም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
46. ጾመኛ መሆኑን ረስቶ የበላ ወይም የጠጣ ሰው ጾሙን ይሙላ። ያበላውና ያጠጣው አላህ ነውና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
47. ዒድን ከዑመር ቢን ኸጧብ - አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና - ጋር ለመስገድ ተገኘሁ። እንዲህም አሉ: "እነዚህ ሁለት ቀናቶች የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ከመጾም የከለከሉት ቀናቶች ናቸው። (እነርሱም) ከጾማችሁ የምትፈቱበት ቀን (ዒድ አልፊጥር) እና ሌላኛው ቀን ደግሞ ከእርዳችሁ የምትበሉበት የሆነው ቀን (ዒደል አድሓ) ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
48. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ተልቢያቸው "ለበይከ አልላሁምመ ለበይክ፣ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣ ኢነልሐምደ ወንኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላ ሸሪከ ለክ" (አላህ ሆይ! ደግሜ ደጋግሜ ለጥሪህ አቤት እላለሁ፤ ምንም ተጋሪ የለህም። ምስጋና ፀጋና ንግስና ለአንተ ብቻ ነው፤ ምንም ተጋሪ የለህም።) የሚል ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
49. ለይለቱል ቀድርን በረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናቶች በጎደሎ ቁጥሮቹ ውስጥ ፈልጓት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
50. በህልማችሁ በመጨረሻዎቹ የረመዳን ሰባት ቀናት ሆና ማየታችሁ ህልማችሁ ከእውነታው ጋር ገጥማለች ብዬ አምናለሁ። ስለዚህ ለይለቱል ቀድርን የሚፈልግ የሆነ ሰው በመጨረሻዎቹ የረመዳን ሰባት ቀናት ውስጥ ይፈልጋት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
51. አላህ ለናንተ የምትመፀውቱበትን ነገር አላደረገላችሁምን? ሁሉም ተስቢሕ (ሱብሓነሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተክቢር (አላሁ አክበር) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተሕሚድ (አልሐምዱሊላህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ ሁሉም ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) ማለት ሶደቃ ነው፤ በመልካም ማዘዝ ሶደቃ ነው፤ ከመጥፎ መከልከል ሶደቃ ነው፤ ከባሌቤታችሁ ጋር ግንኙነት በመፈፀማችሁ ሶደቃ ይገኛል።" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
52. ለአንድ አማኝ ከዱንያ ችግሮቹ መካከል አንዱን ችግሩን ያቀለለለት ሰው አላህም ከትንሳኤ ቀን ችግሮቹ መካከል አንድን ችግሩን ያቀልለታል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
53. እናንተ ሰዎች ሆይ! ወደ አላህ ተመለሱ (ተውበት አድርጉ)፤ እኔ በቀን መቶ ጊዜ ወደርሱ እመለሳለሁ (ተውበት አደርጋለሁ።) - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
54. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በመከራ ወቅት ከምትጮህ፣ ከምትላጭና ልብሷን ከምትቀዳድድ ራሳቸውን አጥርተዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
55. በኑ ኢስራኢሎችን ነቢያቶች ነበሩ ጉዳያቸውን የሚመሩት። አንድ ነቢይ በሞተ ቁጥር ሌላ ነቢይ ይተካ ነበር። ከኔ በኋላም ነቢይ የለም። ምትኮች (ኸሊፋዎች) ይኖራሉም ይበዛሉም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
56. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የረመዿን የመጨረሻዎቹ አስሩ ቀናት የገቡ ጊዜ ሌሊቱን ህያው ሆነው ያሳልፋሉ፤ ቤተሰባቸውንም ያነቃሉ፤ ይበረቱና ሽርጣቸውንም ያጠብቁ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
57. በፈተና ወቅት አላህን ማምለክ ወደኔ እንደመሰደድ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
58. ወንጀልም ሆነ ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱዓ የሚያደርግ አንድም ሙስሊም የለም በዛች ዱዓው ምክንያት አላህ ከሶስት ነገሮች አንዱን የሚሰጠው ቢሆን እንጂ: ወይ የለመነው በፍጥነት ይሰጠዋል ፤ ወይ ልመናው ለመጪው ዓለም መልካም ምንዳ ማደለቢያ ይሆንለታል፤ ወይም የለመነውን ጉዳይ የሚያክል መጥፎ ነገር ከሱ ዞር ያስደርግለታል። " ሶሀቦችም " ስለዚህ (ዱዓእ) እናብዛ?" አሉ። እሳቸውም "(ዱዓእ ካበዛችሁ) የአላህ ስጦታም እጅግ ይበዛል።" አሏቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
59. ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በችግር ወቅት እንዲህ ይሉ ነበር "ላኢላሃ ኢለሏህ አልዐዚሙል ሐሊም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡል ዐርሺል ዐዚም፣ ላኢላሃ ኢለሏሁ ረቡስ-ሰማዋቲ ወረቡል አርዲ ወረቡል ዐርሺል ከሪም" (ትርጉሙም፡ "ከታላቁና ቻይ ከሆነው አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከታላቁ ዐርሽ ጌታ ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም፤ ከሰማያት ጌታ፣ ከምድር ጌታ፣ ከተከበረው ዐርሽ ጌታ አላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም።" ማለት ነው።)
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
60. ነቢዩ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) {የአላህ እርዳታና (መካን) መክፈት በመጣ ጊዜ፤} [አንነስር:1] የሚለው ምዕራፍ በርሳቸው ላይ ከወረደ በኋላ በሚሰግዱት ሶላት ውስጥ ሁሉ "ሱብሓነከ ረብበና ወቢሐምዲከ አልላሁምመግፊርሊ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
61. አንዳችሁ ያዛጋ ጊዜ ሸይጧን ወደ ውስጡ ስለሚገባ በእጁ አፉን ይያዝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
62. አንድ ሙስሊም በሌላ ሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች ስድስት ናቸው።" ለርሳቸውም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ምንድን ናቸው?" ተባሉ። እርሳቸውም "ያገኘኸው ጊዜ ሰላምታን አቅርብለት፤ የጠራህ ጊዜ ጥሪውን አክብር፤ ካንተ ምክርን በፈለገ ጊዜ ምከረው፤ አስነጥሶ አላህን ያመሰገነ ጊዜ "የርሐሙከሏህ" በለው፤ የታመመ ጊዜ ጠይቀው፤ የሞተም ጊዜ ቅበረው። - 4 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
63. ለኩራት ልብሱን የጎተተን ሰው አላህ አይመለከተውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
64. በመሃላው የሙስሊምን ሐቅ ያለአግባብ የወሰደ ሰው አላህ ለርሱ እሳትን ግድ አድርጎበታል፤ ጀነትንም በርሱ ላይ እርም አድርጓል።" አንድ ሰውዬም ለርሳቸው እንዲህ አለ፡ "የአላህ መልክተኛ ሆይ! (የማለበት ጉዳይ) ትንሽም እንኳ ብትሆን (ይቀጣልን)?" እርሳቸውም "የአራክ እንጨት ቢሆን እንኳ! (ይቀጣበታል።)
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
65. አብዛኛው ሰው በነርሱ የከሰረባቸው ሁለት ፀጋዎች አሉ: ጤንነትና ነፃ (ትርፍ) ወቅት
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
66. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ሱጁድ ውስጥ እንዲህ ይሉ ነበር "አላሁመግፊርሊ ዘንቢ ኩለሁ ዲቀሁ ወጂለሁ፣ ወአወለሁ ወአኺረሁ፣ ወዐላኒየተሁ ወሲረሁ"» ትርጉሙም "አላህ ሆይ! ደቂቁንም ትልቁንም፣ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም፣ ግልፁንም፣ ድብቁንም ወንጀሌን ሁሉንም ማረኝ። - 8 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
67. ተራጋሚዎች የትንሳኤ ቀን መስካሪዎችም ሆነ አማላጅ አይሆኑም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
68. ጌታችሁ የሚያፍርና ቸር ነው። ባሪያው የልመና እጆቹን ወደርሱ ከፍ አድርጎ ለምኖት በባዶ መመለስን ያፍራል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
69. ሰዎች አላህን ያላወሱበትና በነቢያቸው ላይ ሶላት ያላወረዱበት መቀማመጥ ከተቀመጡ በነርሱ ላይ ቁጭት ይሆንባቸዋል። ከፈለገ ይቀጣቸዋል ከፈለገም ይምራቸዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
70. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) ጠቅለል ያሉ ዱዓዎችን ማድረግ ይወዱ ነበር። ከዚህ ውጪ ያለውንም ይተዉ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
71. መሃላ ሸቀጥን ተፈላጊ የሚያደርግ (የሚያዋድድ)፤ ትርፍን (በረከት) ደግሞ የሚያጠፋ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
72. ንፋስን አትሳደቡ! የምትጠሉትን ነገር በተመለከታችሁ ጊዜ "አላህ ሆይ! ከዚህች ንፋስ መልካሙን፣ በውስጧ የያዘችውንም መልካም ነገር፣ የታዘዘችውንም መልካም ነገር እንጠይቅሃለን፤ ከዚህች ንፋስ ጉዳት፣ ውስጧ ከያዘችው ጎጂ ነገር፣ ከታዘዘችውም መጥፎ ነገር በአንተ እንጠበቃለን።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
73. አንዳችሁ አላህ ሆይ! ከፈለግክ ማረኝ! ከፈለግክ እዘንልኝ! ከፈለግክ ሲሳይን ለግሰኝ! አይበል። ጥያቄውን ቁርጥ ያድርግ። እርሱ አላህ የሻውን ይሰራልና። ለርሱም አስገዳጅ የለውም። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
74. እርሱ ዘንድ ስሜ ተወስቶ በኔ ላይ ሶላት ያላወረደ ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ረመዷንን አግኝቶ ከዚያም ከመማሩ በፊት የወጣበት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ፤ ወላጆቹን እርጅና ላይ አግኝቶ ጀነት ያላስገቡት ሰው አፍንጫው በአፈር ትታሽ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
75. አመቱን ሙሉ የጾመ አልጾመም። በወር ሶስት ቀን መጾም አመቱን ሙሉ እንደመጾም ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
76. እንዲህ እንዲህ ያሉ ሰዎች ምን ሆነው ነው? እኔ ግን እሰግዳለሁም እተኛለሁም፤ እጾማለሁም አፈጥራለሁም፤ ሴትንም አገባለሁ! ከኔ ፈለግ ውጭ የሰራ ከኔ አይደለም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
77. ሁለት ሙስሊሞች ተገናኝተው በእጅ በመጨባበጥ ሰላምታ ከተለዋወጡ ከመለያየታቸው በፊት ለነርሱ ወንጀላቸው ይማራል። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
78. የሱረቱል ከህፍ መጀመሪያ አስር አንቀጾችን የሸመደደ ሰው ከደጃል ይጠበቃል።" በሌላ ዘገባ "ከሱረቱል ከህፍ መጨረሻ አስር አንቀጾች…
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
79. ሞቱ ያልቀረበን በሽተኛ የጠየቀና እርሱ ዘንድ ሰባት ጊዜ "አስአሉሏሀል ዐዚም ረበል ዐርሺል ዐዚም አንየሽፊከ" ካለ አላህ ከዛ ካመመው በሽታ ያድነዋል።" ትርጉሙም "ታላቁ አላህን የታላቁን ዐርሽ ጌታ እንዲፈውስህ እጠይቃለሁ።" ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
80. የአደም ልጆች ቀልቦች ሁሉ ከአርራሕማን ጣቶች በሁለቱ ጣቶች መካከል ናቸው። (እርሱ ዘንድ ሁሉም ቀልቦች) እንደ አንድ ቀልብ ናቸው። እንደፈለገ ይገለባብጣቸዋል። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
81. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) በሁለት ነገሮች መካከል ምርጫ ሲሰጣቸው ወንጀል እስካልሆነ ድረስ የሚመርጡት ገሩን ነው። ወንጀል ከሆነ ግን ከርሱ እጅግ የሚርቁ ነበሩ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
82. አንዳችን ነገር ከኛ ሰምቶ እንደሰማው አድርጎ ያደረሰ ሰው አላህ ያብራው። ከሰማው ሰው የበለጠ (የሰማውን አብልጦ) የሚጠብቅ ስንትና ስንት ሰው አለ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
83. አላህ የመጀመሪያውንም የመጨረሻውንም ሰዎች አንድ ሜዳ ላይ ይሰበስባል። (ከመጠቅጠቃቸውም የተነሳ) የአንድ ተጣሪ ድምፅ ያሰማቸዋልም፤ አንድ ሰው አዳርሶ መመልከትም ይችላል። ፀሐይም ወደነርሱ ትቀርባለች። ሰዎችም የማይችሉትና የማይቋቋሙት ችግርና ጭንቅ ይደርስባቸዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
84. አማኞች ጀነት ውስጥ ከአንድ ወጥና ውስጡ ባዶ ከሆነ ሉል የተሰራ ድንኳን አላቸው። ርዝማኔውም ስልሳ ማይል ነው። ለአማኞችም በውስጡ ሚስቶች አሏቸው። አንድ አማኝ እነርሱን (ሊገናኝ) ይዞራል። ነገር ግን እርስበርሳቸው አይተያዩም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
85. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን) የሴት ልጅ አለባበስን የሚለብስን ወንድና የወንድ ልጅ አለባበስን የምትለብስ ሴትን ረገሙ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
86. ለርሱ (ለኡዱሒያ) የሚታረድ እርድ ያለው ሰው የዙልሒጃ ጨረቃ የወጣች ጊዜ ኡዱሒያውን እስኪያርድ ድረስ ከፀጉሩም ይሁን ከጥፍሩ አንዳችም እንዳይቆርጥ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
87. ረመዳን የገባ ጊዜ የጀነት በሮች ይከፈታሉ፤ የእሳት በሮችም ይዘጋሉ፤ ሰይጣኖችም ይጠፈነጋሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ