ንዑስ ምድቦች

የሓዲሦች ዝርዝር

1. 'የላቀውና የተከበረው አላህ በአባቶቻችሁ ከመማል ይከለክላችኃል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
2. የትንሳኤ ቀን በሰዎች መካከል መጀመሪያ የሚፈረደው ጉዳይ የደም ጉዳይ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
3. እነርሱ እየተቀጡ ነው። (በናንተ እይታ) ትልቅ በሆነ ወንጀልም አይደለም የሚቀጡት። አንደኛቸው ከሽንት አይጥራራም ነበር። ሌላኛው ደግሞ ነገር በማመላለስ የሚዞር ነበር። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
4. (የአዛንን) ጥሪ በሰማችሁ ጊዜ ሙአዚኑ (አዛን አድራጊው) እንደሚለው በሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
5. እኔ ንፁህ እንደሆነ ነው ያደረግኳቸውና ተዋቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
6. ይህ የደም ስር መቆረጥ ነው። ባይሆን የወር አበባ ስታይበት በነበርሽው የቀናት ልክ ሶላትን ተይ! ከዚያም ታጠቢና ስገጂ።' አሏት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
7. አንዳችሁ ዉዱእ ባደረገ ጊዜ አፍንጫው ውስጥ ውሀ አድርጎ ከዚያም ያውጣው፣ በድንጋይ ያደራረቀ ሰውም (የድንጋዩን ቁጥር) ጎዶሎ ያድርገው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
8. አንድ ሰው ወደ ቤቱ ሲገባ በሚገባበት ወቅትም በሚበላበት ወቅትም አላህን ካወሳ ሰይጣን (ለባልደረቦቹ) 'ማደሪያም እራትም የላችሁም።' ይላል። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
9. ዱንያ ጣፋጭና አረንጓዴ (ለምለም) ናት። አላህም እንዴት እንደምትሰሩ ሊያያችሁ በውስጧ ምትኮች አድርጓችኋል። ዱንያንም ተጠንቀቁ! ሴቶችንም ተጠንቀቁ! - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
10. ከነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) አስር ረከዓዎችን ሸምድጃለሁ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
11. አንዳችሁ ከኢማም በፊት ጭንቅላቱን ቀና ያደረገ ጊዜ አላህ ጭንቅላቱን የአህያ ጭንቅላት እንዳያደርገው ወይም አላህ የሰውነት ቅርፁን የአህያ የሰውነት ቅርፅ እንዳያደርግበት አይፈራምን?!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
12. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጄ በእጃቸው መካከል ሆኖ አንድን የቁርአን ምእራፍ እንደሚያስተምሩኝ ተሸሁድን አስተማሩኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
13. አላህ ሆይ! እኔ ከቀብር ቅጣት፣ ከእሳት ቅጣት፣ ከህይወትና ሞት ፈተና እና ከመሲሕ ደጃል ፈተና ባንተው እጠበቃለሁ።' - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
14. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) መፀዳጃ ቤት የገቡ ጊዜ 'አልላሁመ ኢንኒ አዑዙ ቢከ ሚነል ኹብሢ ወልኸባኢሥ' ይሉ ነበር።" ትርጉሙም "አላህ ሆይ! እኔ ከወንድ ሰይጣንና ከሴት ሰይጣናት በአንተ እጠበቃለሁ።" ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
15. ለወደፊት የምታወግዟቸው ጉዳዮችና አድልዎ ይከሰታል!' ሶሐቦችም 'የአላህ መልክተኛ ሆይ! ምን ያዙናል?' አሉ። እርሳቸውም 'በናንተ ላይ ያለባችሁን ግዴታ ትወጣላችሁ። ለናንተ ያላችሁን ሐቅ ደግሞ ከአላህ ትጠይቃላችሁ።' አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
16. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከጀናባ በሚታጠቡ ጊዜ ሁለት እጃቸውን ይታጠቡና ለሶላት የሚያደርጉትን አምሳያ ዉዱእ ያደርጋሉ። ከዚያም (ሙሉ ገላቸውን) ይታጠቡ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
17. በአላህ ድንበር ላይ በአግባቡ የቆሙና የርሱን ድንበር የሚተላለፉ ሰዎች ምሳሌ በመርከብ ላይ (ቦታ ለመምረጥ) እጣ እንደተጣጣሉ ሰዎች ምሳሌ ነው። (በእጣው መሰረት) ከፊሉን የመርከቡ የላይኛው ክፍል ሲደርሰው ከፊሉን ደግሞ የታችኛው ክፍል ደረሰው። - 8 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
18. መዚይ (ስሜት በሚቀሰቀስ ወቅት የሚወጣ ፈሳሽ ነው።) የሚበዛብኝ ሰው ነበርኩ። ልጃቸው እኔ ዘንድ በመሆኗ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) (ስለብይኑ) መጠየቅ አፈርኩና ሚቅዳድ ቢን አስወድን እንዲጠይቃቸው አዘዝኩትና ጠየቃቸው። እርሳቸውም 'ብልቱን ይታጠብና ዉዱእ ያድርግ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
19. አላህ ከሻ (ከፈለገ) እና እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' አትበሉ። ይልቁንም 'አላህ ከሻ (ከፈለገ) ከዚያም እከሌ ከሻ (ከፈለገ)' በሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
20. 'እስክታምኑ ድረስ ጀነት አትገቡም። እስክትዋደዱ ድረስም አታምኑም። የፈፀማችሁት ጊዜ የምትዋደዱበትን አንዳች ነገር ልጠቁማችሁን? በመካከላችሁ ሰላምታን አሰራጩ።' - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
21. በአላህ መንገድ መታገል ነው።' አሉ። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
22. አንድ ሰውዬ የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ በግራ እጁ በላ። እርሳቸውም 'በቀኝህ ብላ።' አሉት። እርሱም 'አልችልም!' አላቸው። እርሳቸውም 'አያስችልህ!' አሉት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
23. ወደ ቅናቻ የተጣራ ሰው የተከተሉትን ሰዎች አምሳያ ምንዳ ያገኛል። ይህም (ለርሱ የሚሰጠው ምንዳ) ከምንዳቸው አንዳች ሳይቀነስ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
24. 'የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። የገድ እምነት ሺርክ ነው። ከኛ መካከል አንድም የለም በልቡ የገድ እምነት የሚመጣበት ቢሆን እንጂ። ነገር ግን አላህ በርሱ ላይ በመመካታችን ምክንያት ያስወግደዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
25. 'አንተ አለቃችን የሆንክ!' አልን። እርሳቸውም 'የሁሉም አለቃው አላህ ነው።' አሉ። እኛም 'በደረጃ በላጫችን እጅግ ታላቅ የሆንክ!' አልን። እርሳቸውም 'የምትሉትን በሉ ወይም ከምትሉት ከፊሉን በሉ ሰይጣን (ወደ ወሰን ማለፍ እንዳይጎትታቹ) አይጫወትባችሁ' አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
26. 'እናንተ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖት ላይ ወሰን ከማለፍ ተጠንቀቁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች ያጠፋቸው በሃይማኖት ላይ ወሰን ማለፍ ነው።' አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
27. 'አጎቴ ሆይ! በርሷ ምክንያት አላህ ዘንድ የምሟገትልህን ቃል ላኢላሃ ኢለሏህ በል!'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
28. በራሱ የሚተላለፍ ተላላፊ በሽታ የለም፣ ገድም የለም ተስፈኝነት (በጎ ምኞት) ግን ያስደስተኛል።" "አልፈእል (በጎ ምኞት) ምንድነው?" ተባሉ። እርሳቸውም "መልካም ንግግር ነው።" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
29. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ስለ አንሷሮች እንዲህ አሉ: "አማኝ እንጂ አይወዳቸውም፤ ሙናፊቅ እንጂ አይጠላቸውም። አንሷሮችን የወደደ አላህ ይወደዋል። አንሷሮችን የጠላ አላህ ይጠላዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
30. የነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዉዱእ አደራረግ አደረጉላቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
31. 'በእጅህ እንዲህ ብታደርግ በቂህ ነበር።' አሉና ከዚያም በሁለት እጃቸው መሬቱን አንድ ጊዜ መቱ። ከዚያም በግራ እጃቸው ቀኝ እጃቸውን አበሱ። የላይኛውን የመዳፋቸው ክፍልንና ፊታቸውን አበሱ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
32. እኔና ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሁለታችንም ጀናባ ላይ ሆነን ከአንድ እቃ እየጨለፍን እንታጠብ ነበር። የወር አበባ ላይ በሆንኩ ወቅትም ሽርጥ እንዳደርግ ያዙኝና ከግንኙነት ውጪ የሆነን ጨዋታ እንጫወት ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
33. የአላህን መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ እንደሌለ ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ መሆናቸውን በመመስከር፣ ሶላትን በማቋቋም፣ ዘካን በመስጠት፣ መሪዎችን በመስማትና በመታዘዝ ላይ፣ ለሁሉም ሙስሊም ተቆርቋሪ (ታማኝ/ ቅን) በመሆን ላይ ቃል ኪዳን ተጋቧሃቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
34. ጌታችሁን አላህ ፍሩ፣ አምስት (አውቃት) ሶላታችሁን ስገዱ ፣ የፆም ወራችሁን ፁሙ፣ የገንዘባችሁንም ዘካ ስጡ፣ መሪያችሁን ታዘዙ፤ የጌታችሁን ጀነት ትገባላችሁ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
35. ብሰራው ጀነት የምገባበትን ስራ ጠቁሙኝ!' እርሳቸውም እንዲህ አሉት 'በርሱ ላይ አንዳችም ሳታጋራበት አሏህን ማምለክ፣ ግዴታ ሶላትን መስገድ፣ ግዴታ የሆነውን ዘካ መስጠት፣ ረመዷንን መጾም ነው።' - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
36. 'ወንጀላቸውን ይፋ ከሚያደርጉ በስተቀር ሁሉም ህዝቦቼ ይማርላቸዋል። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
37. በምን ጉዳይ ላይ ነው ቃልኪዳን የምንጋባዎት?› አልናቸው። እርሳቸውም ‹አላህን በርሱ አንዳችም ሳታጋሩ በመገዛት፣ በአምስቱ ሶላቶች ላይ፣ በታዛዥነት፣ (ዝግ ባለ ድምፅ የተወሰኑ ቃላቶችን ተናገሩ።) ሰዎችን አንዳችም ነገር ባለመጠየቅ።› አሉን።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
38. ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም ሙሐመድም የአላህ መልክተኛ ናቸው ብለው እስኪመሰክሩ፣ ሶላትን ቀጥ አድርገው እስኪሰግዱና ዘካን እስኪሰጡ ድረስ ሰዎችን እንድጋደል ታዝዣለሁ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
39. የሚጋልብ ሰው ለእግረኛ ሰላምታን ያቅርብ፤ እግረኛ ለተቀማጭ ሰላምታን ያቅርብ፤ ጥቂት ሰዎች በብዙ ሰዎች ላይ ሰላምታን ያቅርቡ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
40. 'ሰውዬው በህብረት የሚሰግደው ሶላት በቤቱ ወይም በሱቁ ከሚሰግደው ሶላት ሀያ ምናምን ደረጃ ትበልጣለች።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
41. የትንሳኤ ቀን የትኛውም ባሪያ እድሜውን በምን እንዳጠፋው፣ በእውቀቱ ምን እንደሰራበት፣ ገንዘቡን ከየት እንዳገኘውና ምን ላይ እንዳዋለው፣ በአካሉ ምን እንዳደረገበት ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
42. 'ንገሩኝ እስኪ! አንዳችሁ በር ላይ በየቀኑ አምስት ጊዜ የሚታጠብበት ወንዝ ቢኖር ይህ ከእድፉ ያስቀራል ትላላችሁን?
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
43. የአማኞች እርስ በርስ የመዋደዳቸው፣ የመተዛዘናቸውና የመራራታቸው ምሳሌ እንደ አንድ የሰውነት ክፍል ነው። ከርሱ አንድ አካል የታመመ ጊዜ የተቀረው ሰውነት በእንቅልፍ እጦትና ትኩሳት ይሰቃያል። - 6 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
44. ልጆቻችሁን ሰባት አመት ሲሆኑ በሶላት እዘዟቸው፤ አስር አመት ሲሞላቸው ሶላት ላለመስገዳቸው ምቷቸው፤ በመካከላቸውም የመኝታ ስፍራቸውን ለዩ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
45. የትንሳኤ ቀን ከመልካም ስነ ምግባር የበለጠ የአማኝን ሚዛን የሚደፋ አንድም ነገር የለም። አላህ ፀያፍ የሚሰራንና ፀያፍ የሚናገርን ይጠላል። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
46. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ወደኛ መጡ። እኛም እንዲህ ብለን ጠየቅናቸው የአላህ መልክተኛ ሆይ! በርሶ ላይ እንዴት ሰላምታ እንደምናቀርብ አውቀናል። በርሶ ላይ ሶላት የምናወርደውስ እንዴት ነው? - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
47. የመጽሐፉን መክፈቻ (ፋቲሓን) ያላነበበ ሰው ሶላት የለውም። - 6 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
48. በሁሉም ውስጥ መልካም ነገር ቢኖርም፤ ጠንካራ ሙእሚን ከደካማው ሙእሚን አላህ ዘንድ የተሻለና ይበልጥ ተወዳጅ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
49. ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) እጅግ አብዝተው ያደርጉት የነበረው ዱዓ 'አልላሁመ ረበና አቲና ፊ ዱንያ ሐሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበን-ናር' የሚለውን ነበር።" (ትርጉሙም: ጌታችን አላህ ሆይ! በዱንያ መልካሙን ስጠን፤ በመጨረሻው ዓለምም መልካሙን ስጠን። ከእሳት ቅጣትም ጠብቀን።) ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
50. የምህረት አጠያየቅ (የኢስቲግፋር) አለቃ - 4 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
51. በደልን ተጠንቀቁ! በደል የትንሳኤ ቀን ድርብርብ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ! ስስት ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች አጥፍቷልና። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
52. አንድ ሰውዬ ነቢዩን (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ማንኛው የኢስላም ክፍል ነው ምርጡ?' ብሎ ጠየቀ። እርሳቸውም 'ምግብ መመገብህ፣ ሰላምታን ባወቅከውም ባላወቅከውም ሰው ላይ ማቅረብህ ነው።' ብለው መለሱለት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
53. ሁላችሁም እረኞች (ሀላፊ) ናችሁ። ስለምትጠብቁት ነገርም ትጠየቃላችሁ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
54. ያ ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታዬ እምላለሁ! ከናንተ በፊት የነበሩትን ህዝቦች መንገድ ትከተላላችሁ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
55. አንድ ሰውዬ ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ዘንድ መጣና በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ አውርቷቸው 'የአላህና የእርሶ መሻት ሆነ።' አለ። ነቢዩም (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) 'ለአላህ ቢጤ አደረግከኝን? የብቸኛው አላህ መሻት ሆነ! በል!' አሉት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
56. የትንሳኤ ቀን አላህ ዘንድ ከሰዎች ሁሉ እጅግ ብርቱ ቅጣት የሚቀጡት እነዚያ በአላህ ፍጥረት የሚፎካከሩት ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
57. 'ሱረቱል ኢኽላስ እና ሁለቱን መጠበቂያዎች (ሱረቱል ፈለቅና ሱረቱን-ናስን) ስታመሽና ስታነጋ ሶስት ጊዜ ካልክ ለሁሉም ነገር ይበቁሃል።' አሉኝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
58. 'ላኢላሃ ኢለሏህ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ፤ አሏሁ አክበር ከቢራ፣ ወልሐምዱሊላሂ ከሢራ፣ ወሱብሓነሏሂ ረቢል ዓለሚን፣ ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐዚዚል ሐኪም በል።' አሉት። - 6 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
59. 'ትልቅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ ግዴታ ሶላት አጋጥሞት ዉዱኡን፣ ተመስጦውንና ሩኩዑን አሳምሮ የሚሰግድ አንድም ሙስሊም የለም፤ ከሶላቷ በፊት የነበረበትን ወንጀል ማስማሪያ ቢሆነው እንጂ፤ ይህም እድሜ ልኩን ነው።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
60. ቁርኣንን የሚቀራ ሙእሚን ምሳሌው እንደ ትርንጎ ነው። ሽታዋም ምርጥ ነው። ጣዕሟም ምርጥ ነው። ቁርአንን የማይቀራ ሙእሚን ምሳሌው እንደ ተምር ነው። ሽታ የላትም ጣዕሟ ግን ጣፋጭ ነው። - 8 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
61. ከሁሉም ግዴታ ሶላቶች በኋላ አስከትሎ የሚላቸው ወይም የሚተገበራቸው የማይከስርባቸው ቃላት: ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተስቢሕ" (ሱብሐነሏህ)፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ "ተሕሚድ" (አልሐምዱ ሊላህ)፣ ሰላሳ አራት ጊዜ "ተክቢራ" (አላሁ አክበር) ማለት ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
62. አዛን ሲባል የሰማ ጊዜ: 'አሽሃዱ አን ላኢላሃ ኢለሏሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለህ ወአነ ሙሐመደን ዐብዱሁ ወረሱሉህ ረዲቱ ቢላሂ ረበን ወቢሙሐመደን ረሱለን ወቢል ኢስላሚ ዲና' ያለ ሰው ወንጀሉ ይማራል።" (ትርጉሙም: ከአላህ በቀር በእውነት የሚመለክ የለም። ብቸኛና አጋር የሌለው ነው። ሙሐመድም የአላህ ባሪያውና መልክተኛው ናቸው ብዬ እመሰክራለሁ፤ በአላህ ጌትነት፣ በሙሐመድ መልክተኝነት፣ በኢስላም ሃይማኖትነት ወድጃለሁ።)
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
63. የአደም ልጅ አስተባበለኝ ይህ ለርሱ አይገባም ነበር! ሰደበኝም ይህም ለርሱ አይገባም ነበር!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
64. ‹የኔን ወዳጅ (ወሊይ) ጠላት አድርጎ የያዘን ሰው በርግጥም ጦርነት እንዳወጀኩበት አሳውቄዋለሁ። ባሪያዬ ግዴታ ካደረግኩበት በበለጠ ወደ እኔ ተወዳጅ በሆነ በአንዳችም ነገር አይቃረብም። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
65. 'ሒርዝ ያንጠለጠለ ሰው በርግጥም አጋርቷል!' አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
66. 'አንድ ሰውዬ ውዱእ አደረገና እግሩ ላይ ጥፍር የምታክል ስፍራ ተወ። ነቢዩ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ተመለከቱትና እንዲህ አሉት: ‹ተመለስና ዉዱእህን አሳምር!› ተመልሶ (አስተካከለና) ከዚያም ሰገደ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
67. 'አሁን ላይ እኔ ያላየኋቸው ሁለት አይነት የእሳት ባለቤቶች አሉ። (እነሱም) ሰዎችን የሚደበድቡበት እንደከብት ጭራ የመሰለ አለንጋ ያላቸው ሰዎች እና ለብሰው የተራቆቱ የሆኑ ራሳቸው ተዘንብለው ሌሎችን ለክፉ የሚጋብዙ፤ ጭንቅላታቸው እንደተዘነበለ የግመል ሻኛ የሆነ ሴቶች ናቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
68. ወንድ ልጅ ወደ ወንድ ልጅ ሀፍረተ ገላ አይመልከት! ሴት ልጅም ወደ ሴት ልጅ ሀፍረተ ገላ አትመልከት!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
69. መላእክት ውሻ እና ቃጭል ካላቸው መንገደኞች ጋር አብረው (አይጎዳኙም) አይሄዱም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
70. ከፀዳን በኋላ የሚወጣንን ድፍርስና ዳለቻ ቀለም ፈሳሽ እንደ ምንም ነገር አንቆጥረውም ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
71. 'የወር አበባሽ የሚያግድሽ ቀናት ያክል (ሳትሰግጂ ሳትፆሚ) ቆዪ ከዚያም ታጠቢ።'
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
72. ለአቅመ አዳም በደረሰ ሰው ላይ ሁሉ የጁሙዓ ቀን መታጠብ፣ ጥርሱን ሊፍቅና ካገኘም ሽቶ መቀባቱ ግዴታ ነው። - 4 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
73. ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱና እጁ (ክፋት) ሰላም የሆኑበት ነው። ሙሃጂር (ስደተኛ) ማለት አላህ የከለከለውን የተወ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
74. 'ሴት ልጅ ከርሷ ጋር ባሏ ወይም ዘመዷ ከሌሉ በቀር ሁለት ቀን የሚያስኬድ መንገድን አትጓዝ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
75. ከሁሉም (ግዴታ) ሶላት በኋላ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያጠራ (ሱብሓነሏህ) ያለ፤ ሰላሳ ሶስት ጊዜ አላህን ያመሰገነ (አልሐምዱ ሊላህ) ያለ፣ ሰላሳ ሶስት ጊዜ ተክቢራ (አላሁ አክበር) ያለ፤ ይህም በድምሩ ዘጠና ዘጠኝ ሲሆን መቶ መሙያውንም "ላኢላሃ ኢለላሁ ወሕደሁ ላሸሪከ ለሁ፣ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዓላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር" ያለ ሰው ወንጀሉ የባህር አረፋ አምሳያ ቢደርስ እንኳ ይማራል። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
76. ከሁሉም ግዴታ ሶላት በኋላ አየተል ኩርሲይን የቀራ ሰው ጀነት ለመግባት ከሞት በቀር ምንም አይከለክለውም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
77. የዚህ ሃይማኖት ጉዳይ ቀንና ምሽት የደረሰበት ስፍራ ሁሉ ይደርሳል። አላህ፤ በሀያሉ ሀይልም ይሁን በውርደታሞች ውርደት ይህንን ሃይማኖት እያንዳንዱ የግንብ (የከተማ) ቤት ውስጥም ይሁን የሳር ቤት (የገጠር ቤት) ውስጥ ሳያስገባው አይቀርም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
78. አንዳችሁ ሶላቱ ውስጥ የተጠራጠረ ጊዜ ሶስት ይሁን አራት ስንት እንደሰገደ ካላወቀ ጥርጣሬውን ይጣልና እርግጠኛ በሆነበት ላይ ይገንባ። ከዛም ከማሰላመቱ በፊት ሁለት ሱጁዶችን ይውረድ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
79. አስካሪ ሁሉ ኸምር ነው። አስካሪ ሁሉ ክልክል ነው። በዚህ ዓለም አስካሪ መጠጥ አዘውትሮ ጠጥቶ ንስሀ ሳይገባ የሞተ ሰው በመጪው ዓለም አይጠጣም። - 6 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
80. የአላህ መልክተኛ ሆይ! በጎ ላደርግለት እጅግ የተገባው ማን ነው?" አልኳቸው። እርሳቸውም "እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም እናትህ ከዚያም አባትህ ከዚያም ቅርብ የሆኑ ዘመዶችህ" አሉ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ