ንዑስ ምድቦች

የሓዲሦች ዝርዝር

1. በተውኳችሁ ላይ ተዉኝ። ከናንተ በፊት የነበሩት ህዝቦች የጠፉት በመጠየቃቸውና ነቢያቶቻቸውን በመቃረናቸው ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
2. በእውነተኝነት ላይ አደራችሁን! እውነተኝነት ወደ መልካም ይመራል። መልካም ነገር ደግሞ ወደ ጀነት ይመራልና። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
3. የቀጭን ሐርንና የወፍራም ሐርን ልብስ አትልበሱ! በወርቅና ብር እቃ አትጠጡ! በ(ወርቅና ብር) ትሪም አትብሉ! እርሷ በዚህ ዓለም ለነርሱ ናት፤ በመጪው ዓለም ደግሞ ለኛ ናት።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
4. መፀዳጃ ቦታ የመጣችሁ ጊዜ ወደ ቂብላ አትዙሩም ጀርባ አትስጡም! ነገር ግን ወደ ምስራቅ ወይም ምዕራብ ዙሩ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
5. አንዳችሁ እየሸና ሳለ ብልቱን በቀኝ እጁ አይያዘው፤ ሲፀዳዳም በቀኝ እጁ አይጥረግ፤ በእቃ ውስጥም አይተንፍስ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
6. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ሶላት በሚከፍቱበት ወቅትና
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
7. 'አልላሁምመ ባዒድ በይኒ ወበይነ ኸጧያየ ከማ ባዐድተ በይነል መሽሪቂ ወልመግሪብ
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
8. የመልካም ጓደኛና የመጥፎ ጓደኛ ምሳሌ እንደ ሽቶ ተሸካሚና እንደወናፍ ነፊ ነው። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
9. ሰውዬው አማኝ ሆኖ ያነጋና ከሀዲ ሆኖ የሚያመሽበት፤ ወይም አማኝ ሆኖ ያመሽና ከሀዲ ሆኖ የሚያነጋበት፤ እምነቱንም በአለማዊ ሸቀጥ እስከመሸጥ የሚያደርሱ የድቅድቅ ጨለማ ቁራጭ የመሰሉ ፈተናዎች ከመምጣታቸው በፊት በመልካም ስራ ተቻኮሉ። - 4 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
10. የአማኝ ነገር ይደንቃል። ሁሉ ነገሩ መልካም ነው። ይህም ለአማኝ እንጂ ለሌላ ለአንድም አካል ሊሆን አይችልም። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
11. የአላህ መልክተኛ (የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና) ያስነጠሱ ጊዜ እጃቸውን ወይም ልብሳቸውን አፋቸው ላይ አድርገው ድምፃቸውን ይቀንሱበት ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
12. በአላህ እምላለሁ! ለአንተ ቀይ ግመል ከሚኖርህ በአንተ ሰበብ አላህ አንድ ሰው ቢመራልህ የተሻለ ነው። - 4 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
13. አላህ ወንጀሎችን የሚሰርዝበትን፣ ደረጃዎችን ከፍ የሚያደርግበትን ነገር አልጠቁማችሁምን? - 6 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
14. በላጩን ሥራችሁ፣ ንጉሳችሁ ዘንድ የጠራችውን ሥራችሁ፣ ደረጃችሁንም ከፍ የምታደርገውን ስራችሁን፣
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
15. ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁመዓ ቀን ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
16. ‹ለአላህ ሱጁድ እንድታበዛ አደራ እልሀለሁ። ለአላህ አንድ ሱጁድ አትወርድም አላህ በርሷ ደረጃህን ከፍ ቢያደርግና ወንጀልህንም የሚሰርዝ ቢሆን እንጂ›
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
17. ሁለቱን የቀዝቃዛ ወቅቶች ሶላት የሰገደ ሰው ጀነት ገባ። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
18. አላህ ዐዘ ወጀል በቀን ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) በምሽት እጁን ይዘረጋል። በምሽት ኃጢዓት የፈፀሙ እንዲፀፀቱ (ተውበት እንዲያደርጉ) ደግሞ በቀን እጁን ይዘረጋል። ይህም ፀሀይ በመግቢያዋ በኩል እስክትወጣ ድረስ ቀጣይ ነው። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
19. ሁሉም የሰው ልጅ መገጣጠሚያ አጥንቶች ምፅዋት አለባቸው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
20. አንዳችሁ ለነፍሱ የሚወደውን ነገር ለወንድሙ እስካልወደደ ድረስ አላመነም። - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
21. የጁመዓ ቀን ልክ እንደ ጀናባ ትጥበት ከታጠበ በኃላ ማልዶ የሄደ ሰው ልክ የግመል ቁርባን እንዳቀረበ ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
22. ምግብ በልቶ ‹አልሐምዱ ሊላሂለዚ አጥዐመኒ ሀዛ ወረዘቀኒሂ ሚን ገይሪ ሐውሊን ሚንኒ ወላቁውዋህ› ያለ ሰው ያሳለፈው ወንጀል ለርሱ ይማርለታል።"» ትርጉሙም "ያለኔ ኃይልና ብልሃት ይህንን ላበላኝና ለለገሰኝ አላህ ምስጋና የተገባው ነው።" ማለት ነው።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
23. ‹የአደም ልጅ ሆይ አንተ እስከለመንከኝና እስከከጀልከኝ ድረስ አንተ ላይ ካለብህ ወንጀልህ ጋርም እምርሃለሁ። (በመማሬም) ምንም አይመስለኝም፤ - 2 ملاحظة
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
24. እናንተ ሰዎች ሆይ! ሰላምታን አስፋፉ፣ ምግብንም አብሉ፣ ዝምድናን ቀጥሉ፣ ሰዎች በተኙበት በሌሊት ስገዱ በሰላም ጀነት ትገባላችሁ።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
25. የእስልምና ሃይማኖት ገር ነው። አንድም ሰው የእስልምናን ሃይማኖት ከመጠን በላይ አያጠብቅም (ሃይማኖቱ) የሚያሸንፈው ቢሆን እንጂ፤ ሚዛናዊ ሁኑ! አቀራርቡ!
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
26. የጋብቻን ጣጣ የቻለ ሰው ያግባ! ጋብቻ አይንን ሰባሪና ብልትን ጠባቂ ነውና። ጋብቻን ያልቻለ ሰው መፆም አለበት። ፆም ለርሱ ማኮላሺያ (የጾታዊ ፍላጎቱን የሚቆርጥለት) ነውና።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
27. ነቢዩ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የአላህ ሶላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈንና ገላቸውን ከአንድ ቁና ውሃ እስከ አምስት እፍኝ ድረስ ባለ ውሃ ያጥቡ ወይም ይታጠቡ ነበር። በአንድ እፍኝ ደግሞ ዉዱእ ያደርጉ ነበር።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
28. መላዕክቶች ውሻና ስዕል ወዳለበት ቤት አይገቡም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
29. ባልደረቦቼን አትሳደቡ፤ ከናንተ መካከል አንዱ የኡሑድን ተራራ አምሳያ የሚያህል ወርቅ ቢመፀውት የአንዳቸውንም እፍኝ ሆነ የእፍኙን ግማሽ የመፀወቱት ጋር አይደርስም።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ
30. አላህ ከኡመቴ በውስጣቸው የሚናገሩትን ነገር እስካልሰሩት ወይም እስካልተናገሩት ድረስ ይቅር ብሏቸዋል።
عربي እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ