عن أبي هريرة رضي الله عنه:
أَنَّ رَجُلًا قَالَ لِلنَّبِيِّ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: أَوْصِنِي، قَالَ: «لَا تَغْضَبْ» فَرَدَّدَ مِرَارًا قَالَ: «لَا تَغْضَبْ».
[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 6116]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተዘገበው እንዲህ አሉ:
አንድ ሰውዬ ለነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አለ: "ምከሩኝ!" እሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት። ጥያቄውን ደጋግሞ መላልሶ ጠየቃቸው እርሳቸውም "አትቆጣ!" አሉት።
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 6116]
ከሰሓቦች አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና አንዱ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አንድ የሚጠቅመውን ነገር እንዲጠቁሙት ፈለገ። እርሳቸውም እንዳይቆጣ አዘዙት። ይህም ማለት ወደቁጣ የሚያነሳሱ ምክንያቶችን እንዲርቅ፣ የሚያስቆጣ ነገር በተከሰተ ጊዜም ነፍሱን እንዲቆጣጠር፣ በቁጣው ወደ መግደል፣ መማታት፣ ስድብና የመሳሰሉት ነገር እንዳይሻገር ማለት ነው።
ሰውዬውም በተደጋጋሚ ምክር እንዲጨምሩለት ፈለገ። ነቢዩም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም "አትቆጣ!" ከምትለው ምክር የዘለለ ምንም አልጨመሩለትም።