عن المِقدام بن معدي كرب رضي الله عنه عن النبي صلى الله عليه وسلم قال:
«إِذَا أَحَبَّ الرَّجُلُ أَخَاهُ فَلْيُخْبِرْهُ أَنَّهُ يُحِبُّهُ».
[صحيح] - [رواه أبو داود والترمذي والنسائي في السنن الكبرى وأحمد] - [سنن أبي داود: 5124]
المزيــد ...
ከሚቅዳም ቢን መዕዲከሪብ እንደተላለፈው ነቢዩ የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይስፈን እንዲህ ብለዋል:
"አንድ ሰው ወንድሙን ከወደደው እንደሚወደው ይንገረው።"
[ሶሒሕ ነው።] - [አቡዳውድ፣ቲርሚዚ፣ ነሳኢ በሱነኑል ኩብራ ፣ አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን አቡዳውድ - 5124]
ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በምእመናን መካከል መስተጋብራቸውን ከሚያጠናክሩና በመካከላቸውም ውዴታን ከሚያሰፍኑ ሰበቦች መካከል አንዱን ጠቀሱ። ይኸውም አንድ ሰው ወንድሙን የሚወደው ከሆነ እንደሚወደው ይንገረው አሉ።