عن معاوية رضي الله عنه قال: سمعت النبي صلى الله عليه وسلم يقول:
«مَنْ يُرِدِ اللهُ بِهِ خَيْرًا يُفَقِّهْهُ فِي الدِّينِ، وَإِنَّمَا أَنَا قَاسِمٌ، وَاللهُ يُعْطِي، وَلَنْ تَزَالَ هَذِهِ الْأُمَّةُ قَائِمَةً عَلَى أَمْرِ اللهِ، لَا يَضُرُّهُمْ مَنْ خَالَفَهُمْ، حَتَّى يَأْتِيَ أَمْرُ اللهِ».
[صحيح] - [متفق عليه] - [صحيح البخاري: 71]
المزيــد ...
ከሙዓዊያህ -አላህ መልካም ሥራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ: ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ሲሉ ሰምቻዋለሁ፦
"አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለትን ሰው ሃይማኖቱን ያስገነዝበዋል። እኔ አከፋፋይ ብቻ ነኝ አላህ ነው የሚሰጠው። ይህች ኡማህ በአላህ ትእዛዝ ላይ የቆመች ከመሆን አትወገድም! የአላህ ትእዛዝ እስክትመጣ ድረስም የተቃረናቸው ሁሉ አይጎዳቸውም።"
[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 71]
አላህ ለእርሱ መልካምን የሻለት ሰው ሃይማኖቱን መገንዘብ እንደሚቸረው፤ ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አላህ ከሰጣቸው ሲሳይ፣ ዕውቀትና ሌሎችም ነገሮች የሚያከፋፍሉና የሚያሰራጩ አከፋፋይ ብቻ እንጂ ትክክለኛው ሰጪ አላህ ብቻ ነው። ከሱ ውጪ ያሉት ከሰበብነት የዘለለ ከርሱ ፈቃድ ውጪ እንደማይጠቅሙ፤ ይህ ኡማህ በአላህ ትእዛዝ ላይ ከመቆም እንደማይወገድና ትንሳኤ እስከሚቆም ድረስም የተፃረራቸው እንደማይጎዳቸው ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተናገሩ።