+ -

عن أبي هريرة رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال:
«كُلُّ أُمَّتِي يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ إِلَّا مَنْ أَبَى»، قَالُوا: يَا رَسُولَ اللهِ، وَمَنْ يَأْبَى؟ قَالَ: «مَنْ أَطَاعَنِي دَخَلَ الْجَنَّةَ، وَمَنْ عَصَانِي فَقَدْ أَبَى».

[صحيح] - [رواه البخاري] - [صحيح البخاري: 7280]
المزيــد ...

ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና-እንደተላለፈው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡
"ሁሉም ህዝቦቼ ጀነት ይገባሉ እምቢ ያለ ሲቀር" ሶሐቦችም "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን እምቢ ይላል?" አሉ። እሳቸውም "እኔን የታዘዘኝ ጀነት ገባ ፤ እኔን ያመፀኝ ደግሞ በርግጥም እምቢ ብሏል።" በማለት መለሱ።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ቡኻሪ ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ አልቡኻሪ - 7280]

ትንታኔ

ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀነት ከመግባት ራሱን ያቀበ ሰው ካልሆነ በስተቀር ሁሉም ህዝባቸው ጀነት እንደሚገቡ ተናገሩ።
ሰሐቦችም አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና "የአላህ መልክተኛ ሆይ! ማን ራሱን ከጀነት ያቅባል?" አሉ።
እሳቸውም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም : "መልክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተከተለና የታዘዘ ጀነት ገባ። ያመፀና ለሸሪዐ ታዛዥ ያልሆነ ሰው ግን በርግጥም በመጥፎ ስራዎቹ ጀነት ከመግባት ራሱን አቅቧል።" በማለት መለሱላቸው።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. መልክተኛውን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መታዘዝ አላህን ከመታዘዝ ይመደባል። እሳቸውን ማመፅም አላህን ከማመፅ ይመደባል።
  2. ነቢዩን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መታዘዝ ጀነት መግባትን ስታስፈርድ እሳቸውን ማመፅ ደግሞ እሳት መግባትን የምታስፈርድ መሆኗ።
  3. ከዚህ ኡማህ አላህና መልክተኛውን ያመፁ ሲቀሩ ነቢዩን ታዛዥ ለሆኑ ብስራት ነው፤ ሁሉም ጀነት ይገባሉና።
  4. ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በኡመታቸው ላይ ያላቸውን እዝነትና እንዲመሩ ያላቸውን ጥልቅ ጉጉት እንረዳለን።
ተጨማሪ