+ -

عن عائشة رضي الله عنها قالت: سمعتُ من رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول في بيتي هذا:
«اللَّهُمَّ مَنْ وَلِيَ مِنْ أَمْرِ أُمَّتِي شَيْئًا فَشَقَّ عَلَيْهِمْ فَاشْقُقْ عَلَيْهِ، وَمَنْ وَلِيَ مِنْ أَمْرِ أُمَّتِي شَيْئًا فَرَفَقَ بِهِمْ فَارْفُقْ بِهِ».

[صحيح] - [رواه مسلم] - [صحيح مسلم: 1828]
المزيــد ...

ከእናታችን ዓኢሻህ -አላህ መልካም ስራዋን ይውደድላትና- እንደተላለፈው እንዲህ አለች: የአላህ መልክተኛን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቤቴ ውስጥ ይህንን ሲሉ ሰምቻለሁ:
"አላህ ሆይ! ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና እነርሱን ለችግር የዳረገ እርሱንም የሚቸገር አድርገው ። ከኡመቴ ጉዳይ በአንዳች ነገር የተሾመና ለነሱ የራራን ለርሱም ራራለት።"

[ሶሒሕ ነው።] - [ሙስሊም ዘግበውታል።] - [ሶሒሕ ሙስሊም - 1828]

ትንታኔ

የሙስሊሞች ጉዳዮች ውስጥ በየትኛውም ትንሽም ይሁን ትልቅ ሹመት ፣ አጠቃላይም ይሁን ቁንፅል ሹመትን የተሾመ ከዚያም ለሙስሊሞች ሳይራራ ችግርን በነርሱ ላይ የሚያባብስባቸው የሆነን ሰው ሁሉ ላይ አላህ በሰራው ስራ ተመሳሳይ እሱንም ለችግር እንዲዳርገው የአላህ መልክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዱዓእ አደረጉበት።
ለነርሱ የራራና ጉዳዮቻቸውን ባቀለለ ላይም አላህ ለርሱ እንዲራራና ጉዳዮቹን እንዲያገራለት ዱዓ አደረጉለት።

ትርጉም: እንግሊዝኛ የኡርዱ ቋንቋ ስፔንኛ ኢንዶኔዥያኛ ኡይጙራዊ ባንጋሊኛ ፈረንሳይኛ ቱርክኛ ሩስያኛ ቦስንያኛ ሲንሃላዊ ህንድኛ ቻይንኛ ፋርስኛ ቬትናማዊ ታጋሎግ ኩርዳዊ ሃውሳ ፖርቹጋልኛ ማላያላምኛ ቴልጉ ስዋሒልኛ ታሚልኛ ቦርምኛ ታይላንድኛ ጀርመንኛ ጃፓንኛ ቡሽትኛ አሳምኛ አልባንኛ السويدية الهولندية الغوجاراتية Kyrgyzisht النيبالية Jorubisht الليتوانية الدرية الصربية الصومالية الطاجيكية Kinjaruandisht الرومانية المجرية التشيكية الموري Malagasisht الفولانية ጣልያንኛ Oromisht Kannadisht الولوف البلغارية Azerisht الأوزبكية الأوكرانية الجورجية اللينجالا المقدونية
ትርጉሞችን ይመልከቱ

ከሐዲሱ የምንጠቀማቸው ቁምነገሮች

  1. ከሙስሊሞች ጉዳዮች መካከል አንድ ነገር ላይ የተሾመ ሰው በቻለው መጠን ለነርሱ መራራት ግዴታው መሆኑን ፤
  2. ምንዳ የሚሰጠን በስራችን አይነት መሆኑን፤
  3. የመራራትና የሀይለኝነት መለኪያ ሚዛኑ ቁርአንና ሐዲሥና ባልተፃረረ መልኩ መሆኑን እንረዳለን።