عن أبي هريرة رضي الله عنه قال:
سُئِلَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ عَنْ أَكْثَرِ مَا يُدْخِلُ النَّاسَ الْجَنَّةَ، فَقَالَ: «تَقْوَى اللهِ وَحُسْنُ الْخُلُقِ»، وَسُئِلَ عَنْ أَكْثَرِ مَا يُدْخِلُ النَّاسَ النَّارَ فَقَالَ: «الْفَمُ وَالْفَرْجُ».
[حسن صحيح] - [رواه الترمذي وابن ماجه وأحمد] - [سنن الترمذي: 2004]
المزيــد ...
ከአቡ ሁረይራ -አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና- እንደተላለፈው እንዲህ አሉ:
የአላህ መልክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በአብዛኛው ሰዎችን ጀነት ስለሚያስገባው ነገር ተጠየቁ፤ እሳቸውም "አላህን መፍራት እና መልካም ስነምግባር ነው።" አሉ። በአብዛኛው ሰዎችን እሳት ስለሚያስገባቸው ነገርም ተጠየቁ። እሳቸውም "ምላስና ብልት ነው።" አሉ።
[ሐሰኑን ሶሒሕ ነው።] - [ቲርሚዚ፣ ኢብኑ ማጀህና አሕመድ ዘግበውታል።] - [ሱነን ቲርሚዚ - 2004]
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጀነት የሚያስገቡ ትልልቅ ምክንያቶች ሁለት መሆናቸውን ገለፁ። እነሱም:
አላህን መፍራትና መልካም ስነምግባር ናቸው።
አላህን መፍራት: በአንተና በአላህ ቅጣት መካከል መጠበቂያ ማድረግህ ነው። ይህም ትእዛዙን በመፈፀምና ክልከላውን በመራቅ ነው።
መልካም ስነምግባር ደሞ: ፊትን ፈታ በማድረግ ፣ መልካምን በመለገስና ከማወክ በመቆጠብ ነው።
እሳት የሚያስገቡት ትልልቅ ምክንያቶች ደግሞ ሁለት ናቸው። እነሱም:
ምላስና ብልት ናቸው።
ከምላስ ወንጀሎች መካከል:- ውሸት፣ ሀሜት፣ ወሬ ማዋሰድና ሌሎችም ናቸው።
ከብልት ወንጀሎች መካከል ደሞ:- ዝሙት፣ ግብረሰዶምና ሌሎችም ይጠቀሳሉ።